ሕዝቅኤል 1:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሕያዋኑ ራስ በላይ የሚያስፈራ፥ ሰማይ የሚመስል፥ እንደ በረዶ የሚያንጸባርቅ፥ በራሳቸው ላይ ተዘርግቶ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሕያዋኑ ፍጡራን ራስ በላይ የሚያስፈራና፤ እንደ በረዶ የሚያንጸባርቅ ጠፈር የሚመስል ነገር ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሕያዋን ከፍጥረቶቹ ራስ በላይ እንደ መስተዋት ከሚያብረቀርቅ የከበረ ድንጋይ የተሠራ ጠፈር የሚመስል ወለል ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእነዚያ እንስሶች ራስ ላይ ያለው መልክ ከላይ በክንፎቻቸው ላይ የተዘረጋ የበረድ መልክ እንዳለበት ጠፈር ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእንስሶች ራስ በላይ የሚያስፈራ በረዶ የሚመስል የጠፈር አምሳያ በራሳቸው ላይ ተዘርግቶ ነበር። |
ከራሳቸው በላይ ካለው ሰማይ በላይ ዙፋን የሚመስል ነበረ፥ እርሱም የሰንፔር ድንጋይ ይመስል ነበር፥ ዙፋን በሚመስለው፥ በላዩ ላይም ሰው የሚመስል ነበረ።
በዙፋኑም ፊት ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባሕር ነበረ። በዙፋኑም መካከል በዙፋኑም ዙሪያ፥ በፊትና በኋላ ዐይኖች የሞሉአቸው አራት ሕያዋን ፍጡራን ነበሩ።