ሕዝቅኤል 1:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሕያዋኑ መንፈስ በመንኮራኩሮቹ ውስጥ ስለ ነበረ ሲሄዱ ይሄዳሉ፥ ሲቆሙ ይቆማሉ፥ ከምድር ሲነሡ መንኮራኩሮቹም በአጠገባቸው ይነሣሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍጡራኑ ሲንቀሳቀሱ ይንቀሳቀሳሉ፤ ፍጡራኑ ቀጥ ብለው ሲቆሙ እነርሱም ይቆማሉ፤ ፍጡራኑ ከምድር ከፍ ከፍ ሲሉ፣ የሕያዋኑ ፍጡራን መንፈስ በውስጣቸው ስላለ መንኰራኵሮቹ ዐብረዋቸው ይነሣሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የፍጥረቶቹ መንፈስ በመንኰራኲሮቹም ውስጥ በመኖሩ ፍጥረቶቹ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ አብረው ይንቀሳቀሳሉ፤ ሲቆሙም አብረው ይቆማሉ፤ ከመሬት ወደ አየር በሚመጥቁበትም ጊዜ፥ አብረው ይመጥቃሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሄዱም ጊዜ ይሄዳሉ፤ በቆሙም ጊዜ ይቆማሉ፤ በእነዚያ መንኰራኵሮች ውስጥ የሕይወት መንፈስ አለና ከምድር በተነሡ ጊዜ መንኰራኵሮቹ ከእነርሱ ጋር ይነሣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእንስሶች መንፈስ በመንኰራኵሮቹ ውስጥ ነበረና እነዚያ ሲሄዱ እነዚህ ይሄዱ ነበር፥ እነዚያም ሲቆሙ እነዚህ ይቆሙ ነበር፥ እነዚያም ከምድር ከፍ ከፍ ሲሉ መንኰራኵሮቹ በአጠገባቸው ከፍ ከፍ ይሉ ነበር። |
የሕያዋኑ መንፈስ በመንኰራኵሮች ውስጥ ስለ ነበረ እነዚህ ሲቆሙ እነዚያም ይቆሙ ነበር፥ እነዚህ ሲነሱ እነዚያም ከእነርሱ ጋር ይነሱ ነበር።