ሕዝቅኤል 1:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 መንፈሱ ወደሚሄድበት ሁሉ እነርሱም ይሄዳሉ፥ የሕያዋኑ መንፈስ በመንኮራኩሮቹ ውስጥ ስለ ነበረ መንኮራኩሮቹም በእነርሱ አጠገብ ይነሡ ነበር። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም20 መንፈስ ወደሚሄድበት ሁሉ ይሄዳሉ፤ የሕያዋኑ ፍጡራን መንፈስ በውስጣቸው ስላለ መንኰራኵሮቹ ዐብረዋቸው ይነሣሉ፤ Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 ፍጥረቶቹ መንፈስ ወደሚሄድበት አቅጣጫ ሁሉ በሚበርሩበት ጊዜ፥ መንኰራኲሮቹም አብረው ይበሩ ነበር፤ ይህም የሆነው የፍጥረቶቹ መንፈስ በመንኰራኲሮቹም ውስጥ ስለ ነበረ ነው። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 ደመና ባለበት በዚያ መንፈስ አለ፤ እንስሶቹ ይሄዳሉ፤ ከእነርሱም ጋር መንኰራኵሮቹ ይነሣሉ፤ የሕይወት መንፈስ በመንኰራኵሮች አለና። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 መንፈሱ ወደሚሄድበት ሁሉ እነርሱ ሄዱ፥ የእንስሶች መንፈስ በመንኰራኵሮቹ ውስጥ ነበረና መንኰራኵሮቹ በእነርሱ አጠገብ ከፍ ከፍ አሉ። Ver Capítulo |