ሕዝቅኤል 1:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕያዋኑም ሲሄዱ መንኮራኩሮቹም በአጠገባቸው ይሄዱ ነበር። እንስሶቹ ከምድር ሲነሱ መንኮራኩሮቹም ይነሱ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕያዋኑ ፍጡራን ሲንቀሳቀሱ፣ በአጠገባቸው ያሉ መንኰራኵሮችም ይንቀሳቀሱ ነበር፤ ሕያዋኑ ፍጡራን ከምድር ከፍ ከፍ ሲሉ፣ መንኰራኵሮቹም ዐብረዋቸው ከፍ ከፍ ይሉ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍጥረቶቹ በተንቀሳቀሱ ቊጥር መንኰራኲሮቹ አብረዋቸው ይንቀሳቀሱ ነበር፤ ፍጥረቶቹ ከምድር ተነሥተው ከፍ በሚሉበትም ጊዜ መንኰራኲሮቹ አብረው ከፍ ይሉ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሄዱም ጊዜ ሠረገላዎች ከእነርሱ ጋር ይሄዳሉ። እንስሶቹም ከምድር ሲነሡ መንኰራኵሮቹም ከእነርሱ ጋር ይነሣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንስሶቹም በሄዱ ጊዜ መንኰራኵሮቹ በአጠገባቸው ሄዱ። እንስሶቹም ከምድር ከፍ ከፍ ባሉ ጊዜ መንኰራኵሮቹ ከፍ ከፍ አሉ። |
ኪሩቤልም ሲሄዱ መንኰራኵሮቹ በአጠገባቸው ይሄዱ ነበር፥ ኪሩቤል ከምድር ለመነሣት ክንፎቻቸውን ሲዘረጉ መንኰራኵሮቹም ከአጠገባቸው አይለዩም ነበር።
ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ዘረጉ፥ እኔም እያየሁ ከምድር ተነሡ፥ ሲወጡም መንኰራኵሮች በአጠገባቸው ነበሩ፥ በጌታ ቤት በምሥራቁ በር መግቢያ ቆሙ፥ የእስራኤል አምላክ ክብርም በላያቸው ላይ ነበረ።