ሕዝቅኤል 1:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመንኰራኵሩም መልክና አሠራር የቢረሌ መልክ ይመስል ነበር፥ የአራቱም መልክ አንድ ዓይነት ነበር፥ መልካቸውና አሠራራቸው በመንኰራኵር መካከል ያለ መንኰራኵር ይመስል ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የመንኰራኵሮቹ መልክና አሠራር እንዲህ ነበር፤ እንደ ቢረሌ ያንጸባርቁ ነበር፤ የአራቱም ቅርጽ ተመሳሳይ ሆኖ፤ እያንዳንዱ መንኰራኵር በመንኰራኵር ውስጥ ተሰክቶ የተሠራ ይመስል ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አራቱም መንኰራኲሮች ተመሳሳይ ነበሩ፤ እያንዳንዱም እንደ ከበረ ዕንቊ ያንጸባርቅ ነበር፤ እንዲሁም እያንዳንዱ አንዱ መንኰራኲር በሌላው መንኰራኲር ውስጥ የሚተላለፍ ይመስል ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመንኰራኵሩም መልክ እንደ ቢረሌ ነበረ፤ አራቱም አንድ አምሳያ ነበሩ፤ ሥራቸውም በመንኰራኵር ውስጥ እንዳለ መንኰራኵር ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የመንኰራኵሩም መልክ እንደ ቢረሌ ነበረ፥ አራቱም አንድ አምሳያ ነበሩ፥ ሥራቸውም በመንኰራኵር ውስጥ እንዳለ መንኰራኵር ነበረ። |
በዚህም ብዙ ልዩ ልዩ የእግዚአብሔር ጥበብ አሁን በቤተ ክርስቲያን በኩል በሰማያዊ ስፍራ ውስጥ ላሉት አለቆችና ሥልጣናት እንድትታወቅ ነው።