ዘፀአት 9:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የፈርዖንም ልብ ጸና፤ ጌታም በሙሴ አፍ እንደ ተናገረ የእስራኤልን ልጆች አልለቀቀም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ የፈርዖን ልብ ደነደነ፤ እግዚአብሔር ለሙሴ እንደ ተናገረውም እስራኤላውያን ይሄዱ ዘንድ አልለቀቃቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አስቀድሞ በሙሴ አማካይነት ተናግሮ እንደ ነበረ ንጉሡ ልቡን አደንድኖ እስራኤላውያንን አለቀቀም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የፈርዖንም ልብ ጸና፤ እግዚአብሔርም በሙሴ አፍ እንደ ተናገረ የእስራኤልን ልጆች አልለቀቀም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የፈርዖንም ልብ ጸና፤ እግዚአብሔርም በሙሴ አፍ እንደተናገረ የእስራኤልን ልጆች አልለቀቀም። |
ጌታም ሙሴን አለው፦ “ወደ ግብጽ ስትመለስ በእጅህ ያደረግሁትን ተአምራት ሁሉ ተመልከት በፈርዖንም ፊት ታደርጋቸዋለህ፤ እኔም ልቡን አጸናዋለሁ፥ ሕዝቡንም አይለቅቅም።