ንጉሡ ኢዮርብዓም “እባክህ እጄን ያድንልኝ ዘንድ ወደ አምላክህ ወደ ጌታ ጸልይልኝ!” ሲል የእግዚአብሔርን ነቢይ ለመነው። የእግዚአብሔርም ነቢይ ወደ ጌታ ጸልዮለት የንጉሡ እጅ ዳነች፤ እንደ ቀድሞም ሆነች።
ዘፀአት 9:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአምላክ ነጎድጓድ በረዶውም በዝቶአልና ወደ ጌታ ጸልዩ፤ እለቅቃችኋለሁ፥ ከዚህ በኋላ እዚህ አትቀመጡም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም መብረቅና በረዶ በዝቶብናልና ወደ እግዚአብሔር ጸልዩልን፤ እንድትሄዱ እለቃችኋለሁ፤ ከዚህ በኋላ በዚህ የመኖር ግዴታ የለባችሁም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በረዶውና ነጐድጓዱ እጅግ ስለ በዛብን ወደ እግዚአብሔር ጸልዩልን፤ በእርግጥ እለቃችኋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲህ እዚህ የምትቈዩበት ጊዜ አይኖርም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩልኝ፤ የአምላክ ነጐድጓድ፥ በረዶውም፥ እሳቱም ጸጥ ይላል፤ እኔም እለቅቃችኋለሁ፤ ከዚያም በኋላ ከዚህ አትቀመጡም” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአምላክ ነጎድጓድ በረዶውም በዝቶአልና ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ፤ እለቅቃችሁማለሁ፤ ከዚያም በኋላ በዚህ አትቀመጡም፤” አላቸው። |
ንጉሡ ኢዮርብዓም “እባክህ እጄን ያድንልኝ ዘንድ ወደ አምላክህ ወደ ጌታ ጸልይልኝ!” ሲል የእግዚአብሔርን ነቢይ ለመነው። የእግዚአብሔርም ነቢይ ወደ ጌታ ጸልዮለት የንጉሡ እጅ ዳነች፤ እንደ ቀድሞም ሆነች።
ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “በፈርዖንና በግብጽ ላይ ገና አንድ መቅሰፍት አመጣለሁ፥ ከዚያ በኋላ ከዚህ ይለቅቃችኋል፤ ሲለቅቃችሁም ሙሉ በሙሉ ያባርራችኋል።
ሙሴም፦ “እነሆ እኔ ከአንተ ዘንድ እወጣለሁ፥ የዝንቡም መንጋ ከፈርዖን፥ ከአገልጋዮቹና ከሕዝቡ ነገ እንዲሄዱ ወደ ጌታ እጸልያለሁ፤ ነገር ግን ለጌታ ይሠዋ ዘንድ ሕዝቡን እንዳይለቅቅ ፈርዖን እንደገና አያታልለን” አለ።
ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን ጠርቶ “እንቁራሪቶቹን ከእኔና ከሕዝቤ እንዲያርቅ ወደ ጌታ ጸልዩልኝ፤ ለጌታም እንዲሠዋ ሕዝቡን እለቅቃለሁ” አላቸው።
“የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ይወጋናልና ስለ እኛ፥ እባክህ፥ ጌታን ጠይቅ፤ ምናልባትም ጌታ ለእኛ እንደ ተአምራቱ ሁሉ አድርጐ ከእኛ እንዲመለስ ያደርገዋልና።”
ሕዝቡም ወደ ሙሴ መጥተው እንዲህ አሉት፦ “በጌታና በአንተ ላይ ስለ ተናገርን ኃጢአት ሠርተናል፤ እባቦቹን ከእኛ እንዲያርቅልን ወደ ጌታ ጸልይልን።” ሙሴም ስለ ሕዝቡ ጸለየ።
ሕዝቡም ሁሉ ሳሙኤልን፥ “ሌላው በደላችን ሳያንስ፥ ንጉሥ እንዲነግሥልን በመጠየቃችን ተጨማሪ ክፋት ስላደረግን እንዳንሞት፥ ለአገልጋዮችህ ወደ አምላክህ ወደ ጌታ ጸልይልን” አሉት።