ዘፀአት 9:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከፈርዖን አገልጋዮች የጌታን ቃል የፈራ አገልጋዮቹንና ከብቶቹን ወደ ቤቶቹ አሸሸ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔርን ቃል የፈሩት የፈርዖን ሹማምት፣ ባሮቻቸውንና ከብቶቻቸውን ለማስገባት ተጣደፉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከንጉሡ ባለሟሎች አንዳንዶቹ እግዚአብሔር ስለ ተናገረው ነገር በፍርሃት ተጨነቁ፤ ስለዚህም አገልጋዮቻቸውና እንስሶቻቸው ወደ ቤት ተሰብስበው እንዲጠለሉ አደረጉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከፈርዖን ሹሞች የእግዚአብሔርን ቃል የፈራ ከብቶቹን ወደ ቤቶቹ ሰበሰበ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከፈርዖንም ባሪያዎች የእግዚአብሔርን ቃል የፈራ ባሪያዎቹንና ከብቶቹን ወደ ቤቶቹ አሸሸ፤ |
ኖኅ ገና ስለማይታየው ነገር ተረድቶ እግዚአብሔርን እየፈራ ቤተ ስዎቹን ለማዳን መርከብን በእምነት አዘጋጀ፤ በዚህም ዓለምን ኰነነ፤ በእምነትም የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።