ዘፀአት 9:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከምድጃውም አመድ ወስደው በፈርዖን ፊት ቆሙ፤ ሙሴም ወደ ሰማያት በተነው፥ በሰውና በእንስሳ ላይም ፈሳሽ የሚያወጣ ብጉንጅ ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ከምድጃው ዐመድ ወስደው በፈርዖን ፊት ቆሙ፤ ሙሴም ወደ ሰማይ በተነው፤ መግል የያዘ ዕባጭም በሰዎችና በእንስሳት ላይ ወጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ጥቂት ዐመድ ከምድጃ ወስደው በንጉሡ ፊት ቆሙ፤ ሙሴም ወደ አየር በበተነው ጊዜ ሕዝቡና እንስሶቹ በብርቱ ቊስል ተመቱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም አመዱን በፈርዖን ፊት ወስዶ ወደ ሰማይ በተነው፤ በሰውና በእንስሳም ላይ ሻህኝ የሚያወጣ ቍስል ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከምድጃውም አመድ ወስደው በፈርዖን ፊት ቆሙ፤ ሙሴም ወደ ሰማይ በተነው፤ በሰውና በእንስሳም ላይ ሻህኝ የሚያወጣ ቍስል ሆነ። |