La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 9:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ወደ ፈርዖን ግባ እንዲህም በለው የዕብራውያን አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘እንዲያገለግሉኝ ሕዝቤን ልቀቅ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ወደ ፈርዖን ሂድና እንዲህ በለው፤ ‘የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ “ያመልኩኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ወደ ንጉሡ ሄደህ የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይልሃል በለው፦ ‘ያገለግለኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ወደ ፈር​ዖን ገብ​ተህ እን​ዲህ በለው፦ የዕ​ብ​ራ​ው​ያን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ያመ​ል​ኩኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን ልቀቅ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፤ ወደ ፈርዖን ዘንድ ገብተህ ንገረው፤ ‘የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያገለግሉኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።

Ver Capítulo



ዘፀአት 9:1
7 Referencias Cruzadas  

ሙሴና አሮንም ወደ ፈርዖን ገቡ፥ እንዲህም አሉት፦ “የዕብራውያን አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘በፊቴ እራስህን ለማዋረድ እስከ መቼ እንቢ ትላለህ? እንዲያገለግሉኝ ሕዝቤን ልቀቅ።


እነርሱም ቃልህን ይሰማሉ፤ አንተና የእስራኤል ሽማግሌዎች ወደ ግብጽ ንጉሥ ትሄዳላችሁ፦ ‘የዕብራውያን አምላክ ጌታ ተገለጠልን፤ ስለዚህ ለአምላካችን ለጌታ እንድንሠዋ የሦስት ቀን መንገድ በምድረ በዳ እንሂድ’ ትሉታላችሁ።


ከዚህም በኋላ ሙሴና አሮን ሄደው ፈርዖንን እንዲህ አሉት፦ “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘በምድረ በዳ በዓል እንዲያደርግልኝ ሕዝቤን ልቀቅ።’”


ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አሮንን ‘በትርህን ይዘህ እጅህን በፈሳሾቹ በወንዞቹና በኩሬዎቹ ላይ እጅህን ዘርጋ፥ በግብጽም ምድር ላይ እንቁራሪቶችን አውጣ’ በለው።”


ጌታም እንዲሁ አደረገ፤ በፈርዖን ቤት፥ በአገልጋዮቹም ቤቶች ውስጥ ብዙ የዝንብ መንጋ መጣ፤ በግብጽም ምድር ሁሉ ላይ፤ ከዝንቡ መንጋ የተነሣ ምድር ተበላሸች።


ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ማልደህ ተነሣ፥ በፈርዖንም ፊት ቁም እንዲህም በለው፦ የዕብራውያን አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘እንዲያገለግሉኝ ሕዝቤን ልቀቅ።