ዘፀአት 8:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አሮንን ‘በትርህን ይዘህ እጅህን በፈሳሾቹ በወንዞቹና በኩሬዎቹ ላይ እጅህን ዘርጋ፥ በግብጽም ምድር ላይ እንቁራሪቶችን አውጣ’ በለው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን አለው፤ “ወደ ፈርዖን ዘንድ ሄደህ፣ እንዲህ በለው፤ ‘እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ “እኔን ያመልኩኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ወደ ፈርዖን ሄደህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ንገረው፤ ‘ያገለግለኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ወደ ፈርዖን ግባ፤ እንዲህም በለው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያመልኩኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን ተናገረው፤ “ወደ ፈርዖን ግባ፤ እንዲህም በለው፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ ‘ያገለግለኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ። |
እርሱም፦ “እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እኔም እንደ ላክሁህ ምልክትህ ይህ ይሆናል፤ ሕዝቡን ከግብጽ ባወጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ እግዚአብሔርን ታገለግላላችሁ” አለ።
እነርሱም ቃልህን ይሰማሉ፤ አንተና የእስራኤል ሽማግሌዎች ወደ ግብጽ ንጉሥ ትሄዳላችሁ፦ ‘የዕብራውያን አምላክ ጌታ ተገለጠልን፤ ስለዚህ ለአምላካችን ለጌታ እንድንሠዋ የሦስት ቀን መንገድ በምድረ በዳ እንሂድ’ ትሉታላችሁ።
ከዚህም በኋላ ሙሴና አሮን ሄደው ፈርዖንን እንዲህ አሉት፦ “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘በምድረ በዳ በዓል እንዲያደርግልኝ ሕዝቤን ልቀቅ።’”
እነርሱም፦ “የዕብራውያን አምላክ ተገናኘን፤ የሦስት ቀን መንገድ በምድረ በዳ እንድንሄድ፥ ለጌታ ለአምላካችን እንድንሠዋ እንለምንሃለን ካልሆነ ተላላፊ በሽታ ወይም ሰይፍ እንዳይጥልብን” አሉት።
እንዲህም ትለዋለህ፦ ‘ጌታ የዕብራውያን አምላክ፦ በምድረ በዳ እንዲያገለግሉኝ ሕዝቤን ልቀቅ፥ ብሎ ወደ አንተ ላከኝ፤ እነሆ አንተ እስከ ዛሬ አልሰማህም።
ጌታም እንዲሁ አደረገ፤ በፈርዖን ቤት፥ በአገልጋዮቹም ቤቶች ውስጥ ብዙ የዝንብ መንጋ መጣ፤ በግብጽም ምድር ሁሉ ላይ፤ ከዝንቡ መንጋ የተነሣ ምድር ተበላሸች።
ጌታ ኢያሱን እንዲህ አለው፦ “ጋይን በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁና በእጅህ ያለውን ጦር በእርሷ ላይ ዘርጋ፤” ኢያሱም በእጁ ያለውን ጦር በከተማይቱ ላይ ዘረጋ።