La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 4:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ይህንንም ተአምራት የምታደርግበትን በትር በእጅህ ይዘኸው ትሄዳለህ።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ታምራዊ ምልክት እንድታሳይባት ይህችን በትር በእጅህ ይዘህ ሂድ።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ተአምራት የምታሳይበትንም ይህን በትር ይዘህ ሂድ።”

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ይህ​ች​ንም ተአ​ም​ራት የም​ታ​ደ​ር​ግ​ባ​ትን በትር በእ​ጅህ ያዝ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ይህችንም ተአምራት የምታደርግባትን በትር በእጅህ ይዘሃት ሂድ።”

Ver Capítulo



ዘፀአት 4:17
8 Referencias Cruzadas  

ኤልሳዕም ወደ ግያዝ መለስ ብሎ “በፍጥነት ተነሥና የእኔን ምርኲዝ ይዘህ ሂድ! ለአንድም ሰው ሰላምታ ለመስጠት እንኳ በመንገድ አትቁም፤ ማንም ሰው ሰላምታ ቢሰጥህ አጸፋውን ለመመለስ ጊዜ አታጥፋ፤ በቀጥታ ወደ ቤት ሄደህ የእኔን ምርኲዝ በልጁ ፊት ላይ አኑር!” አለው።


አንተም በትርህን አንሣ፥ እጅህንም በባህሩ ላይ ዘርጋ፥ ክፈለውም፤ የእስራኤልም ልጆች በባህሩ ውስጥ በደረቅ ምድር ያልፋሉ።


ሙሴም ኢያሱን፦ “ሰዎችን ምረጥልን፥ ከአማሌቅም ጋር ለመዋጋትም ውጣ፤ እኔ ነገ የእግዚአብሔርን በትር በእጄ ይዤ በኮረብታው ጫፍ ላይ እቆማለሁ” አለው።


ጌታም፦ “ይህ በእጅህ ያለው ምንድነው?” አለው። እርሱም፦ “በትር ነው” አለ።


ሙሴም ሚስቱንና ልጆቹን ወሰደ፥ በአህያ ላይም አስቀመጣቸው፥ ወደ ግብጽም ምድር ተመለሰ፤ ሙሴም የእግዚአብሔርን በትር ይዞ ሄደ።


“በትሩን ውሰድ፤ አንተና ወንድምህ አሮን ማኅበሩን ሰብስቡ፥ እነርሱም ዓይናቸው እያየ ድንጋዩ ውኃን እንዲሰጥ ተናገሩት፤ ለእነርሱም ከድንጋዩ ውኃ ታወጣላቸዋለህ፤ እንዲሁም ለማኅበሩና ለከብቶቻቸው የሚጠጣ ወኃ ትሰጣቸዋለህ።”


ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱንም ነገር ያሳፍር ዘንድ እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤