እንዲሁም በዚያኑ ቀን ከቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ያለውን አደባባይ መካከለኛ ክፍል ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን አደረገ፤ ቀጥሎም በሙሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ የእህል ቁርባንና የኅብረት መሥዋዕት፥ የእንስሶች ስብ ሁሉ ለእግዚአብሔር አቀረበ፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት ከነሐስ የተሠራው መሠዊያ ይህን ሁሉ መሥዋዕት መያዝ ስለማይችል ነው።
ዘፀአት 39:39 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የናሱን መሠዊያ፥ የናሱን መከታ፥ መሎጊያዎቹንና ዕቃዎቹን ሁሉ፥ የመታጠቢያውን ሳሕንና ማስቀመጫው፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የንሓስ መሠዊያው ከንሓስ መጫሪያው፣ መሎጊያዎቹና ዕቃዎቹ ሁሉ ጋራ፤ የመታጠቢያው ሳሕን ከነማስቀመጫው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከነሐስ የተሠራው መሠዊያ ከነሐስ ከተሠራው መከላከያው ጋር፥ መሎጊያዎቹና የእርሱ መገልገያ ዕቃዎች ሁሉ፥ የመታጠቢያው ሳሕንና ማስቀመጫው፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የናሱንም መሠዊያ፥ የናሱንም መከታ፥ መሎጊያዎቹንም፥ ዕቃውንም ሁሉ፥ የመታጠቢያውን ሰንም፥ መቀመጫውንም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የናሱንም መሠዊያ፥ የናሱንም መከታ፥ መሎጊያዎቹንም፥ ዕቃውንም ሁሉ፥ የመታጠቢያውን ሰንም መቀመጫውንም፤ |
እንዲሁም በዚያኑ ቀን ከቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ያለውን አደባባይ መካከለኛ ክፍል ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን አደረገ፤ ቀጥሎም በሙሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ የእህል ቁርባንና የኅብረት መሥዋዕት፥ የእንስሶች ስብ ሁሉ ለእግዚአብሔር አቀረበ፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት ከነሐስ የተሠራው መሠዊያ ይህን ሁሉ መሥዋዕት መያዝ ስለማይችል ነው።
“ርዝመቱ አምስት ክንድ፥ ወርዱ አምስት ክንድ የሆነ መሠዊያ ከግራር እንጨት ሥራ፤ መሠዊያው አራት ማዕዘን ይሁን፤ ከፍታው ሦስት ክንድ ይሁን።
የአደባባዩን መጋረጃዎች፥ ምሰሶዎቹን፥ እግሮቹን፥ የአደባባዩን ደጃፍ መጋረጃ፥ አውታሮቹን፥ ካስማዎቹን፥ ለመገናኛው ድንኳን ለማደሪያው የመገልገያ ዕቃዎች ሁሉ፥