በጨረሱም ጊዜ የተረፈውን ገንዘብ በንጉሡና በዮዳሄ ፊት አመጡ፤ በእርሱም ለጌታ የቤት ዕቃ፥ የአገልግሎትና የቁርባን ዕቃ፥ ሙዳዮቹም፥ የወርቅና የብርም ዕቃ ተሠራበት። በዮዳሄም ዘመን ሁሉ በጌታ ቤት የሚቃጠል መሥዋዕት ሁልጊዜ ያቀርቡ ነበር።
ዘፀአት 36:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴንም፦ “ሕዝቡ ጌታ እንዲሠራ ላዘዘው ሥራ ከበቂ በላይ አመጡ” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴንም፣ “ሕዝቡ እግዚአብሔር እንዲሠራ ላዘዘው ሥራ ከበቂ በላይ እያመጡ ነው” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሕዝቡ እግዚአብሔር ላዘዘው ሥራ ከሚያስፈልገው በላይ እጅግ ብዙ ስጦታ በማምጣት ላይ ናቸው” አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ለሙሴ፥ “እግዚአብሔር ይደረግ ዘንድ ላዘዘው ሥራ ከሚበቃ በላይ እጅግ የሚበልጥ ሕዝቡ አመጡ” ብለው ነገሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ሙሴን፦ እግዚአብሔር ለማገልገያ ሥራ ይደረግ ዘንድ ላዘዘው ከሚበቃ ይልቅ እጅግ የሚበልጥ ሕዝቡ አመጡ ብለው ተናገሩት። |
በጨረሱም ጊዜ የተረፈውን ገንዘብ በንጉሡና በዮዳሄ ፊት አመጡ፤ በእርሱም ለጌታ የቤት ዕቃ፥ የአገልግሎትና የቁርባን ዕቃ፥ ሙዳዮቹም፥ የወርቅና የብርም ዕቃ ተሠራበት። በዮዳሄም ዘመን ሁሉ በጌታ ቤት የሚቃጠል መሥዋዕት ሁልጊዜ ያቀርቡ ነበር።
ሙሴም በሰፈሩ ውስጥ አዋጅ እንዲተላለፍ አዘዘ፦ “ወንድ ወይም ሴት ለመቅደሱ ስጦታ ከእንግዲህ ወዲህ አያምጣ”፤ ሕዝቡም እንዳያመጡ ተከለከሉ።