ዘፀአት 32:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሌዊም ልጆች ሙሴ እንዳለ አደረጉ፤ በዚያ ቀን ከሕዝቡ ሦስት ሺህ ሰዎች ሞቱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሌዋውያኑ ሙሴ እንዳዘዛቸው ፈጸሙ፤ በዚያም ዕለት ከሕዝቡ ሦስት ሺሕ ያህል ዐለቁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌዋውያንም ለቃሉ ታዛዦች በመሆን በዚያን ቀን ሦስት ሺህ ሰው ገደሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሌዊም ልጆች ሙሴ እንዳለ አደረጉ፤ በዚያም ቀን ከሕዝቡ ሦስት ሺህ ሰዎች ሞቱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሌዊም ልጆች ሙሴ እንዳለ አደረጉ፤ በዚያም ቀን ከሕዝቡ ሦስት ሺህ ሰዎች ሞቱ። |
እንዲህም አላቸው፦ “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘እያንዳንዱ ሰው ሰይፉን በወገቡ ላይ ይታጠቅ፥ በሰፈሩ ውስጥ ከበር እስከ በር ወዲህ ወዲያ ተመላለሱ፥ ሰው ሁሉ ወንድሙን፥ ሰው ሁሉ ወዳጁን፥ ሰው ሁሉ ጎረቤቱን ይግደል’”
ከእስራኤል ልጆች ርስት ለሌዋውያን የምትሰጡአቸውን ከተሞች እንዲሁ ስጡ፤ ከብዙዎቹ ብዙ፥ ከጥቂቶቹ ጥቂት ትወስዳላችሁ፤ እያንዳንዱ እንደ ወረሱት እንደ ርስታቸው መጠን ከከተሞቻቸው ለሌዋውያን ይሰጣሉ።”