ዘፀአት 32:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)27 እንዲህም አላቸው፦ “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘እያንዳንዱ ሰው ሰይፉን በወገቡ ላይ ይታጠቅ፥ በሰፈሩ ውስጥ ከበር እስከ በር ወዲህ ወዲያ ተመላለሱ፥ ሰው ሁሉ ወንድሙን፥ ሰው ሁሉ ወዳጁን፥ ሰው ሁሉ ጎረቤቱን ይግደል’” Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም27 ከዚያም፣ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ ‘እያንዳንዱ ሰው በወገቡ ላይ ሰይፍ ይታጠቅ፤ በሰፈር ውስጥ ከዳር እዳር እየተመላለሰ እያንዳንዱ ወንድሙን፣ ጓደኛውንና ጎረቤቱን ይግደል’ ” አላቸው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም27 እንዲህም አላቸው፦ “እያንዳንዳችሁ ሰይፋችሁን መዛችሁ ከዚህ በር እስከ ወዲያኛው በር ድረስ በሰፈሩ ውስጥ በመመላለስ ያለ ምንም ምሕረት ወንድሞቻችሁን፥ ወዳጆቻችሁንና ጐረቤቶቻችሁን እንድትገድሉ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር አዞአችኋል።” Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)27 እርሱም፦ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እያንዳንዱ ሰይፉን በወገቡ ላይ ይታጠቅ፤ ሂዱና በሰፈሩ ውስጥ ከበር እስከ በር ተመላለሱ፤ እያንዳንዱም ወንድሙን፥ እያንዳንዱም ጎረቤቱን፥ እያንዳንዱም የቅርቡን ይግደል” አላቸው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)27 እርሱም፦ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእናንተ ሰው ሁሉ ሰይፉን በወገቡ ላይ ይታጠቅ፥ በሰፈሩም ውስጥ በዚህና በዚያ ከበር እስከ በር ተመላለሱ፥ የእናንተም ሰው ሁሉ ወንድሙን ወዳጁንም ጎረቤቱንም ይግደል አላቸው። Ver Capítulo |