ዘፀአት 30:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰው ሥጋ ላይ አይፍሰስ፤ እንደ እርሱ የተሠራ ሌላ ቅባት አትስሩ፤ ቅዱስ ነው፥ ለእናንተም ቅዱስ ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማንም ሰው ሰውነት ላይ አታፍስሱት፤ በተመሳሳይ መንገድ ምንም ዘይት አትሥሩ፤ የተቀደሰ ነው፤ ቅዱስ መሆኑን ልብ በሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማንኛውም ተራ ሰው ላይ አይፍሰስ፤ ይህንንም የመሰለ ቅባት ለመሥራት በዚህ ዘዴ ከመጠቀም ተጠንቀቁ፤ ቅዱስ ስለ ሆነ እናንተም ቅድስናውን ዕወቁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሌላ ሰው ሥጋ ላይ አይፍሰስ፤ እንደ እርሱም የተሠራ ሌላ ቅብዐት አታድርጉ፤ ቅዱስ ነው፤ ለእናንተም ቅዱስ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሰው ሥጋ ላይ አይፍሰስ፤ እንደ እርሱም የተሰራ ሌላ ቅብዓት አታድርጉ፤ ቅዱስ ነው፥ ለእናንተም ቅዱስ ይሁን። |
“በራሱም ላይ የቅባዓት ዘይት የፈሰሰበት፥ የክህነትም ልብስ እንዲለብስ የተቀደሰው፥ ከወንድሞቹ ይበልጥ ከፍ ያለው ካህን የራሱን ጠጉር አያጐስቁል ልብሱንም አይቅደድ።