ዘፀአት 30:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘ይህ በትውልዳችሁ ሁሉ ለእኔ የተቀደሰ የቅባት ዘይት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለእስራኤላውያን ንገራቸው፤ ‘በሚመጡት ትውልዶች ሁሉ ይህ የእኔ የተቀደሰ የቅብዐት ዘይት ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእስራኤልም ሕዝብ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘ይህ የተቀደሰ የቅባት ዘይት ለሚመጡት ዘመናት ሁሉ ለእኔ አገልግሎት ይዋል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተም ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፤ ይህ ለልጅ ልጃችሁ የተቀደሰ የቅብዐት ዘይት ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተም ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ይህ ለልጅ ልጃችሁ የተቀደሰ የቅብዓት ዘይት ይሁንልኝ። |
በመሠዊያው ላይ ካለው ደምና ከቅባት ዘይት ወስደህ በአሮንና በልብሱ ላይ፥ ከእርሱም ጋር በልጆቹና በልብሶቻቸው ላይ ትረጨዋለህ፤ እርሱና ልብሶቹ፥ ከእርሱም ጋር ልጆቹና ልብሶቻቸው ይቀደሳሉ።
“በራሱም ላይ የቅባዓት ዘይት የፈሰሰበት፥ የክህነትም ልብስ እንዲለብስ የተቀደሰው፥ ከወንድሞቹ ይበልጥ ከፍ ያለው ካህን የራሱን ጠጉር አያጐስቁል ልብሱንም አይቅደድ።