ዘፀአት 30:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ መገናኛው ድንኳን በሚገቡበት ጊዜ ወይም ለጌታ የእሳት መሥዋዕት ሊያቃጥሉ ወደ መሠዊያው ለማገልገል በሚቀርቡበት ጊዜ እንዳይሞቱ በውኃ ይታጠቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ መገናኛው ድንኳን በሚገቡበት ጊዜ ሁሉ እንዳይሞቱ በውሃ ይታጠቡ፤ እንዲሁም ለእግዚአብሔር የእሳት መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ መሠዊያው ለማገልገል በሚቀርቡበት ጊዜ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ማድረግ ያለባቸው ወደ ድንኳኑ ከመግባታቸውና የሚቃጠል መሥዋዕት ከማቅረባቸው በፊት ነው፤ ይህንንም ካደረጉ ከሞት ይድናሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ምስክሩ ድንኳን በገቡ ጊዜ፥ ለእግዚአብሔርም የእሳት መሥዋዕት ያቃጥሉ ዘንድ ወደ መሠዊያው ሊያገለግሉ በቀረቡ ጊዜ እንዳይሞቱ ይታጠቡበታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ መገናኛው ድንኳን በገቡ ጊዜ፥ ለእግዚአብሔርም የእሳት መስዋዕት ያቃጥሉ ዘንድ ወደ መሠዊያው ሊያገለግሉ በቀረቡ ጊዜ፥ እንዳይሞቱ ይታጠቡበታል። |
ሰባት ቀን ያልቦካ ቂጣ ትበላላችሁ፤ በመጀመሪያው ቀን ከቤቶቻችሁ እርሾ ታስወግዳላችሁ፤ ከመጀመሪያውም ቀን አንሥቶ እስከ ሰባተኛው ቀን የቦካ የሚበላ ያቺ ነፍስ ከእስራኤል ተለይታ ትጥፋ።
የተቀደሰውን የበፍታ ቀሚስ ይልበስ፥ የበፍታውም ሱሪ በገላው ላይ ይሁን፥ በመርገፍም የተጌጠውን የበፍታው መታጠቂያ ይታጠቅ፥ የበፍታውንም መጠምጠሚያ ይጠምጥም፤ እነዚህ የተቀደሱ ልብሶች ናቸው፤ ገላውንም በውኃ ታጥቦ ይልበሳቸው።
ጌታም ከቤትሼሜሽ ሰዎች ጥቂቱን መታ፤ ምክንያቱም ወደ ጌታ ታቦት ውስጥ በመመልከታቸው ነበር። ከመካከላቸው ሰባ ሰዎችን ገደለ፤ ጌታ እጅግ ስለ መታቸውም ሕዝቡ አለቀሱ።