ንጉሡም አለቃውን ዮዳሄን ጠርቶ እንዲህ አለው፦ “የጌታ ባርያ ሙሴ ስለ ምስክሩ ድንኳን የእስራኤል ጉባኤ እንዲያወጣ ያዘዘውን ግብር ከይሁዳና ከኢየሩሳሌም ላይ ሌዋውያን እንዲሰበስቡ ለምን አላተጋሃቸውም?”
ዘፀአት 30:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የማስተስረያውን ገንዘብ ከእስራኤል ልጆች ወስደህ ለመገናኛው ድንኳን አገልግሎት ስጠው፤ ለእስራኤል ልጆች ለነፍሳችሁ ቤዛ እንዲሆን በጌታ ፊት መታሰቢያ ይሆናል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የማስተስረያውን ገንዘብ ከእስራኤላውያን ተቀብለህ ለመገናኛው ድንኳን አገልግሎት አውለው፤ ለሕይወታችሁ ማስተስረያ በማድረግ በእግዚአብሔር ፊት የእስራኤላውያን ማስተስረያ ይሆናል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን መባ ከእስራኤል ሕዝብ ሰብስበህ ለተቀደሰው ድንኳን መንከባከቢያ እንዲውል አድርግ፤ ይህም መባ ለሕይወታቸው ቤዛ ይሆናል፤ እኔም እጠብቃቸው ዘንድ እነርሱን አስታውሳለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የማስተስረያውንም ገንዘብ ከእስራኤል ልጆች ወስደህ ለምስክሩ ድንኳን ማገልገያ ትሰጠዋለህ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ለነፍሳችሁ ቤዛ እንዲሆን ለእስራኤል ልጆች መታሰቢያ ይሁን።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የማስተስረያውንም ገንዘብ ከእስራኤል ልጆች ወስደህ ለመገናኛው ድንኳን ማገልገያ ታደርገዋለህ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ለነፍሳችሁ ቤዛ እንዲሆን ለእስራኤል ልጆች መታሰቢያ ይሁን። |
ንጉሡም አለቃውን ዮዳሄን ጠርቶ እንዲህ አለው፦ “የጌታ ባርያ ሙሴ ስለ ምስክሩ ድንኳን የእስራኤል ጉባኤ እንዲያወጣ ያዘዘውን ግብር ከይሁዳና ከኢየሩሳሌም ላይ ሌዋውያን እንዲሰበስቡ ለምን አላተጋሃቸውም?”
በቆሬና በእርሱም ተከታዮች ላይ የደረሰው እንዳይደርስበት፥ ከአሮን ልጆች ያልሆነ ሌላ ሰው በጌታ ፊት ዕጣንን ለማጠን እንዳይቀርብ፥ ጌታ በሙሴ እንደ ተናገረው፥ ለእስራኤል ልጆች መታሰቢያ አደረጋቸው።