ዘፀአት 28:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለት የወርቅ ቀለበቶች ሠርተህ በኤፉዱ ፊት ለፊት ባለው በደረት ኪሱ በሁለቱ ጫፎች ላይ ታደርጋቸዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁለት የወርቅ ቀለበቶች አበጅተህ ከኤፉዱ ቀጥሎ ባለው በውስጠኛ ጠርዝ ላይ፣ በሌላ በኩል ካሉት ሁለት የደረት ኪስ ጐኖች ጋራ አያይዛቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደገናም ሁለት የወርቅ ቀለበቶች ሠርተህ በውስጥ በኩል ከኤፉዱ ቀጥሎ ባለው የደረት ኪስ ከታችኛዎቹ ማእዘኖች ጋር እንዲገጣጠሙ አድርግ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለት የወርቅ ቀለበቶችንም ሥራ፤ እነርሱንም ልብሰ መትከፉ በውስጥ በሚያልፍበት በከንፈሩ በኩል በሁለቱ የልብሰ እንግድዓ ጫፎች ላይ ታኖራቸዋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለት የወርቅ ቀለበቶችም ሥራ፥ እነርሱንም በኤፉዱ ፊት ለፊት ባለው በደረቱ ኪስ በሁለቱ ጫፎች ላይ ታደርጋቸዋለህ። |
በተጨማሪም ሁለት የወርቅ ቀለበቶች ሥራ፥ በኤፉዱም ፊት ለፊት ከትከሻዎቹ በታች በብልሃት ከተጠለፈ ከኤፉዱ ቋድ በላይ በመያዣው አጠገብ ታደርጋቸዋለህ።
ኤፉድ ይለብስ የነበረውም አኪያ በመካከላቸው ነበር። እርሱም በሴሎ የጌታ ካህን የነበረው የዔሊ ልጅ፥ የፊንሐስ ልጅ የኢካቦድ ወንድም የአኪጦብ ልጅ ነበር። ሕዝቡም ዮናታን አለመኖሩን አላወቁም ነበር።