ዘፀአት 28:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአራተኛው ረድፍ ቢረሌ፥ መረግድ፥ ኢያስጲድ፤ በወርቅ ፈርጥ ይቀመጣሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአራተኛውም ረድፍ ቢረሌ፣ መረግድና ኢያሰጲድ አድርግበት፤ በወርቅ ፈርጥም ክፈፋቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአራተኛው ረድፍ ቢረሌ፥ መረግድና ኢያስጲድ በወርቅ ፈርጥ ላይ ይቀመጣሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አራተኛውም ተራ ወርቃማ ድንጋይ፥ ቢረሌ፥ ሶም በየተራቸው በወርቅ የተለበጡና የታሠሩ ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአራተኛውም ተራ ቢረሌ፥ መረግድ፥ ኢያስጲድ በወርቅ ፈርጥ ይደረጋሉ። |
የመንኰራኵሩም መልክና አሠራር የቢረሌ መልክ ይመስል ነበር፥ የአራቱም መልክ አንድ ዓይነት ነበር፥ መልካቸውና አሠራራቸው በመንኰራኵር መካከል ያለ መንኰራኵር ይመስል ነበር።
እኔም አየሁ፥ እነሆ በኪሩቤል አጠገብ አራት መንኰራኵሮች ነበሩ፥ አንድ መንኰራኵር በአንድ ኪሩብ፥ አንድ መንኰራኵር በአንድ ኪሩብ አጠገብ ነበረ። የመንኰራኵሮቹም መልክ የቢረሌ ድንጋይ ይመስል ነበር።