ፈርጦችን ከወርቅ ሥራ፤
የወርቅ ፈርጦችን አብጅ፤
ሁለት የወርቅ ፈርጦች ሥራ፤
ፈርጦችንም ከጥሩ ወርቅ ሥራ፤
የወርቅም ፈርጦች ሁለትም ድሪዎች ከጥሩ ወርቅ ሥራ፤ እንደ ተጎነጎነም ገመድ አድርግ፤ የተጎነጎኑትንም ድሪዎች በፈርጦቹ ላይ አንጠልጥል።
በቅርጽ ሠራተኛ ሥራ እንደ ማኅተም ቅርጽ አድርገህ የእስራኤልን ልጆች ስም በሁለት ድንጋዮች ቅረጽ በወርቅ ፈርጥ ሥራቸው።
እንደ ተጎነጎነ ገመድ አድርገህ ሁለት ድሪዎች ከንጹሕ ወርቅ ሥራ፤ የተጎነጎኑትንም ድሪዎች ከፈርጦቹ ጋር አያይዛቸው።
ሁለት የወርቅ ፈርጦችና ሁለት የወርቅ ቀለበቶች ሠሩ፤ ሁለቱንም ቀለበቶች በደረቱ ኪስ በሁለቱ በኩል አደረጉት።
የደረቱን ኪስ ብልህ ሠራተኛ እንደሠራው እንደ ኤፉዱ አሠራር ከወርቅ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃና ከተፈተለ ጥሩ በፍታ ሠራው።