ዘፀአት 27:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአራቱም ማዕዘን ቀንዶችን አድርግለት፥ ቀንዶቹም ከእርሱ ጋር ወጥ ሆነው የተሠሩ ይሁኑ፤ በነሐስም ለብጠው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀንዶቹና መሠዊያው አንድ ወጥ ይሆኑ ዘንድ በአራቱም ማእዘኖች ላይ ቀንድ አድርግለት፤ መሠዊያውንም በንሓስ ለብጠው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአራቱም ማእዘን ጫፍ ላይ ጠርበህ ቀንድ መሳይ ጒጦች አውጣ፤ ይህም ከመሠዊያው ጋር አብሮ የተሠራ ይሁን፤ እርሱም በነሐስ የተለበጠ ይሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአራቱም ማዕዘን ቀንዶችን ታደርጋለህ፤ ቀንዶቹ ሥረ-ወጥ ይሁኑ፤ በናስም ለብጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአራቱም ማዕዘን ቀንዶችን ታደርጋለህ፥ ቀንዶቹም ከእርሱ ጋር በአንድ የተሠሩ ይሁኑ፤ በናስም ለብጠው። |
በአንድ በኩል የአዶንያስ ደጋፊ፥ በሌላ በኩል ደግሞ የአቤሴሎም ተቃዋሚ የሆነው ኢዮአብ የተፈጸመውን ነገር ሁሉ ሰማ፤ ስለዚህም ሸሽቶ ወደ ጌታ ድንኳን ሄደ፤ በዚያም የመሠዊያውን ቀንዶች ይዞ ተማጠነ።
እንዲሁም በዚያኑ ቀን ከቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ያለውን አደባባይ መካከለኛ ክፍል ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን አደረገ፤ ቀጥሎም በሙሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ የእህል ቁርባንና የኅብረት መሥዋዕት፥ የእንስሶች ስብ ሁሉ ለእግዚአብሔር አቀረበ፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት ከነሐስ የተሠራው መሠዊያ ይህን ሁሉ መሥዋዕት መያዝ ስለማይችል ነው።
ከነሐስ ተሠርቶ ለእግዚአብሔር የተለየውም መሠዊያ በዚያ አዲስ መሠዊያና በቤተ መቅደሱ መካከል ነበር፤ አካዝም ያንን መሠዊያ አስነሥቶ እርሱ ባሠራው በአዲሱ መሠዊያ በስተ ሰሜን በኩል አኖረው፤
ከዚያም በኋላ በጌታ ፊት ወዳለው ወደ መሠዊያው ይወጣል፤ ለእርሱም ያስተሰርይለታል፤ ከወይፈኑም ደም ከፍየሉም ደም ወስዶ በመሠዊያው ዙሪያ ያሉትን ቀንዶች ያስነካል።
በመገናኛውም ድንኳን ውስጥ በጌታ ፊት ባለው በመሠዊያው ቀንዶች ላይ ከደሙ ያደርጋል፤ ደሙንም ሁሉ በመገናኛው ድንኳን ደጅ ባለው የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ በታች ያፈስሳል።
ካህኑም ከኃጢአት መሥዋዕት ደም በጣቱ ወስዶ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ ቀንዶች ላይ ያደርገዋል፤ የተረፈውንም ደም የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ በታች ያፈስሳል።
ካህኑም በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በጌታ ፊት ባለው መዐዛው ያማረ ዕጣን በሚታጠንበት መሠዊያ ቀንዶች ላይ ከደሙ ያደርጋል፤ የተረፈውንም የወይፈኑን ደም ሁሉ በመገናኛው ድንኳን ደጅ ባለው የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ በታች ያፈስሳል።
አረደውም፤ ሙሴም ደሙን ወስዶ በጣቱ የመሠዊያውን ቀንዶች ዙሪያ ቀባ፥ መሠዊያውንም አነጻው፤ ደሙንም ከመሠዊያው በታች አፈሰሰው፥ እንዲያስተሰርይለትም ቀደሰው።
የሠራዊት ጌታ ይጠብቃቸዋል፤ እነርሱም ይውጧቸዋል፥ በድንጋይ ወንጭፍም ያሸንፋሉ፤ ይጠጧቸዋል፥ በወይን ጠጅ እንደ ሰከረ ሰው ይሞቃቸዋል፤ እንደ መሠዊያም ማዕዘኖች፥ እንደ ጥዋዎቹም የተሞሉ ይሆናሉ።
ታቦቱንም፥ ገበታውንም፥ መቅረዙንም፥ መሠዊያዎቹንም፥ ካህናቱም የሚገለገሉባቸውን የመቅደሱን ዕቃዎች፥ መጋረጃውንም፥ መገልገያውንም ሁሉ ይጠብቃሉ።
ይሄውም እግዚአብሔር ሊዋሽ በማይቻል በሁለት በማይለወጥ ነገር፥ በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት እንዲሆንልን ነው።