ዘፀአት 26:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከማደሪያውም በላይ ለመሸፈኛ የሚሆኑ መጋረጆች ከፍየል ጠጉር ሥራ፤ ዐሥራ አንድ መጋረጆች ትሠራለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ማደሪያ ድንኳኑን ከላይ ሆነው የሚሸፍኑ በጠቅላላ ዐሥራ አንድ የፍየል ጠጕር መጋረጃዎች ሥራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከፍየል ጠጒር የተሠሩ ዐሥራ አንድ መጋረጃዎችን ለድንኳኑ ክዳን አድርግ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከማደሪያውም በላይ ለድንኳን የሚሆኑ መጋረጃዎች ከፍየል ጠጕር አድርግ፤ ዐሥራ አንድ መጋረጃዎች ታደርጋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከማደሪያውም በላይ ለድንኳን የሚሆኑ መጋረጆች ከፍየል ጠጉር አድርግ፤ አሥራ አንድ መጋረጆች ታደርጋለህ። |
“ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ግምጃ የተሠሩ ዐሥር መጋረጆች ያሉበትን ድንኳን ሥራ፤ ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ ኪሩቤል በእነርሱ ላይ ይሁኑ።
ከዚያም ጌታ በጽዮን ተራራ ላይና በዚያ በሚሰበሰቡትም ሁሉ ላይ በቀን ደመናንና ጢስን፤ በሌሊትም የሚንበለበለውን የእሳት ብርሃን ይፈጥራል፤ በክብሩ ሁሉ ላይ መጋረጃ ይሆናል፤
የማደሪያውን መጋረጆች፥ የመገናኛውንም ድንኳን፥ መደረቢያውን፥ በእርሱም ላይ ያለውን የአቆስጣውን ቁርበት መሸፈኛ፥ የመገናኛውንም ድንኳን ደጃፍ መጋረጃ፥
እንዲሁም እናንተ ጐልማሶች! ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን እንደ ልብስ ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታኑ ግን ጸጋን ይሰጣል” ተብሎ ተጽፎአልና።