La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 25:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሁለት ኪሩቤል ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ፥ በስርየት መክደኛውም ላይ በሁለት ወገን ታደርጋቸዋለህ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በስርየት መክደኛው ዳርና ዳር ላይ የሚሆኑ ከወርቅ የተቀረጹ ሁለት ኪሩቤል ሥራ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከተቀጠቀጠም ወርቅ ክንፎች ያሉአቸው የሁለት ኪሩቤል ምስል ሥራ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሁለት ኪሩ​ቤል ከተ​ቀ​ጠ​ቀጠ ወርቅ ሥራ፤ በስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ውም ላይ በሁ​ለት ወገን ታደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሁለት ኪሩቤል ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ፥ በስርየት መክደኛውም ላይ በሁለት ወገን ታደርጋቸዋለህ።

Ver Capítulo



ዘፀአት 25:18
15 Referencias Cruzadas  

አዳምንም ካስወጣው በኋላ፥ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና በሁሉም አቅጣጫ የምትውለበለብ ነበልባላዊ ሰይፍን በዔድን ገነት በስተ ምሥራቅ አስቀመጠ።


ለዕጣኑም መሠዊያ ንጹሑን ወርቅ በሚዛን፥ ክንፎቻቸውንም ዘርግተው የጌታን ቃል ኪዳን ታቦት የሸፈኑትን የኪሩቤልን የወርቅ ሠረገላ ንድፈ ሐሳብ ሰጠው።


በቅድስተ ቅዱሳንም ውስጥ ከእንጨት ሥራ ሁለቱን ኪሩቤል ሠራ፥ በወርቅም ለበጣቸው።


ከንጹሕ ወርቅ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱ አንድ ክንድ ተኩል የሆነ የስርየት መክደኛ ሥራ።


አንዱን ኪሩብ በአንድ በኩል፥ ሁለተኛውንም ኪሩብ በሌላው በኩል አኑር፥ በስርየት መክደኛው ላይ ኪሩቤል በሁለት በኩል ላይ ታደርጋቸዋለህ።


እንቡጦቹና ቅርንጫፎቹ ከእርሱ ይሁኑ፤ ሁሉም ወጥ ሆኖ ከተቀጠቀጠ ከንጹሕ ወርቅ ይሠሩ።


በፍታም የለበሰውን ሰው እንዲህ አለው፦ በመንኰራኵሮች መካከል ከኪሩብ በታች ግባ፥ ከኪሩቤልም መካከል ካለው እሳት ፍም እጆችህን ሙላ በከተማይቱም ላይ በትናት ብሎ ተናገረው። እኔም እያየሁ ገባ።


እነዚህ በኮበር ወንዝ ከእስራኤል አምላክ በታች ያየኋቸው ሕያዋን ናቸው፥ እኔም ኪሩቤል እንደ ነበሩ አስተዋልሁ።


ሰውዬው ሲገባ ኪሩቤል በቤቱ በደቡብ በኩል ቆመው ነበር፥ ደመናውም ውስጠኛውን አደባባይ ሞላው።


በላይዋም ማስተስሪያውን የሚጋርዱ የክብር ኪሩቤል ነበር፤ ስለ እነዚህም በዝርዝር የመናገሪያው ሰዓት አሁን አይደለም።


ስለዚህ ሕዝቡ ሰዎችን ወደ ሴሎ ልከው፥ በኪሩቤል መካከል በዙፋኑ ላይ የተቀመጠውን የሠራዊት ጌታን የኪዳን ታቦት አስመጡ፤ ሁለቱ የዔሊ ልጆች ሖፍኒና ፊንሐስ ከኪዳኑ ታቦት ጋር በዚያ ነበሩ።