ዘፀአት 24:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም ወደ ተራራው ወጣ፥ ደመናውም ተራራውን ሸፈነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴ ወደ ተራራ ሲወጣ ደመናው ተራራውን ሸፈነ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም ወደ ሲና ተራራ ወጣ፤ ተራራውንም ደመና ሸፈነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም ከኢያሱ ጋር ወደ ተራራ ወጣ፤ ደመናውም ተራራውን ሸፈነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም ወደ ተራራ ወጣ፥ ደመናውም ተራራውን ሸፈነው። |
እንዲህም ሆነ በሦስተኛው ቀን ማለዳ ነጎድጓድ፥ መብረቅና ከባድ ደመና እጅግም የበረታ የቀንደ መለከት ድምጽ በተራራው ላይ ሆነ፤ በሰፈሩ የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተንቀጠቀጡ።
ጌታም ሙሴን፦ “ከአንተ ጋር ስነጋገር ሕዝቡ እንዲሰሙና ለዘለዓለም እንዲያምኑህ፥ እነሆ በከባድ ደመና እመጣለሁ” አለው። ሙሴም የሕዝቡን ቃል ለጌታ ነገረ።
እርሱም ገና እየተናገረ ሳለ እነሆ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ እነሆ ከደመናው ውስጥ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የተወደደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት” የሚል ድምፅ መጣ።