ዘፀአት 23:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጉቦን አትቀበል፤ ጉቦ የሚያዩ ሰዎችን ያሳውራልና፥ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ጕቦ አትቀበል፤ ጕቦ አጥርተው የሚያዩትን ሰዎች ዐይን ያሳውራል፤ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎች ትክክለኛ የሆነውን ነገር እንዳያዩ ዐይናቸውን ስለሚያሳውርና የንጹሕ ሰዎችንም ፍርድ ስለሚያጣምም ጉቦ አትቀበል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መማለጃን አትቀበል፤ መማለጃ የዐይናማዎችን ዐይን ያሳውራልና፥ እውነተኛ ቃልንም ያጣምማልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማማለጃን አትቀበል፤ ማማለጃ የዓይናማዎችን ሰዎች ዓይን ያሳውራልና፥ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና። |
ከንቱውን መባ አታቅርቡ፤ ዕጣናችሁን እጸየፋለሁ፤ የወር መባቻ በዓላችሁን፤ ሰንበቶቻችሁን፤ ጉባኤያችሁንና በክፋት የተሞላውን ስብሰባችሁን መታገሥ አልቻልሁም።
ገዥዎችሽ ዐመፀኞችና የሌባ ግብረ ዐበሮች ናቸው፤ ሁሉም ጉቦን ይወዳሉ፤ እጅ መንሻንም በብርቱ ይፈልጋሉ፤ አባት ለሌላቸው አይቆሙም፤ የመበለቶችንም አቤቱታ አይሰሙም።
በጽድቅ የሚሄድ ቅን ነገርንም የሚናገር፥ በጭቆና የሚገኝ ትርፍን የሚጸየፍ፥ መማለጃን ከመጨበጥ እጁን የሚሰበስብ፥ ደም ማፍሰስን ከመስማት ጆሮቹን የሚከልል፥ ክፋትንም ከማየት ዐይኖቹን የሚጨፍን ነው።
ደም ለማፍሰስ በአንቺ ውስጥ ጉቦን ተቀበሉ፥ አንቺም አራጣና ትርፍ ወስደሻል፥ ጎረቤቶችሽንም ጨቁነሽ የማይገባ ትርፍ አገኘሽ፥ እኔንም ረሳሽኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ጻድቁን የምታሠቃዩ፥ ጉቦንም የምትቀበሉ፥ በበሩም አደባባይ የችግረኛውን ፍርድ የምታጣምሙ እናንተ ሆይ! በደላችሁ እንዴት እንደ በዛ፥ ኃጢአታችሁም እንዴት እንደ ጸና እኔ አውቃለሁና።
እጆቻቸው ክፉ ለማድረግ የተለማመዱ ናቸው፤ ልዑሉና ፈራጁ ጉቦን ይፈልጋሉ፥ ትልቁም ሰው እንደ ነፍሱ ምኞት ይናገራል፤ እንዲሁም ክፋትን ይጐነጉናሉ።
ምክንያቱም ጌታ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ፥ የጌቶችም ጌታ፥ ታላቅ አምላክ፥ ኃያልም፥ የሚያስፈራም፥ በፍርድ የማያደላ፥ ጉቦም የማይቀበል ነው።
እነሆ፤ ከፊታችሁ ቆሜአለሁ፤ በእግዚአብሔርና እርሱ በቀባው ፊት መስክሩብኝ፤ የማንን በሬ ወሰድሁ? የማንን አህያ ወሰድሁ? ማንን አታለልሁ? በማንስ ላይ ግፍ ሠራሁ? አይቶ እንዳላየ ለመሆንስ ከማን እጅ ጉቦ ተቀበልሁ? ከእነዚህ ሁሉ አንዱን እንኳ አድርጌ ከሆነ እመልስላችኋለሁ።”