ዘፀአት 21:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጉድጓዱ ባለቤት ዋጋውን ለባለቤቱ ይክፈል፤ የሞተውም ለእርሱ ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጕድጓዱ ባለቤት ኪሳራ ይክፈል፤ ለባለቤቱ መክፈል አለበት፤ የሞተውም እንስሳ ለርሱ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእንስሳውን ዋጋ ይክፈል፤ ገንዘቡን ለእንስሳው ባለቤት ከከፈለ በኋላ የሞተውን እንስሳ ለራሱ ያስቀር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጕድጓዱ ባለቤት ዋጋቸውን ለባለቤታቸው ይክፈል፤ የሞተውም ለእርሱ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጕድጓዱ ባለቤት ዋጋቸውን ለባለቤታቸው ይክፈል፤ የሞተውም ለእርሱ ይሁን። |
የአንድ ሰው በሬ የሌላውን በሬ ቢወጋ፥ ቢሞትም፥ በሕይወት ያለውን በሬ ይሽጡ፥ ዋጋውንም እኩል ይካፈሉት፤ የሞተውንም ደግሞ እኩል ይካፈሉ።