La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 21:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በሬው ወንድ ባርያ ወይም ሴት ባርያ ቢወጋ፥ የበሬው ባለቤት ሠላሳ የብር ሰቅል ለጌታው ይስጥ፥ በሬው ግን ይወገር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አንድ በሬ ወንድ ወይም ሴት ባሪያን ቢወጋ ባለቤቱ ሠላሳ የብር ሰቅል ለባሪያው ጌታ መክፈል አለበት፤ በሬውም በድንጋይ ይወገር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በሬው ወንድ ወይም ሴት ባሪያ ወግቶ ቢገድል የበሬው ባለቤት ለባሪያው ጌታ ሠላሳ ብር ይክፈለው፤ በሬውም በድንጋይ ተወግሮ ይሙት።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በሬው ወንድ ባሪያ ወይም ሴት ባሪያ ቢወጋ፥ የበ​ሬው ባለ​ቤት ሠላሳ የብር ሰቅል ለጌ​ታ​ቸው ይስጥ፤ በሬ​ውም ይወ​ገር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በሬው ወንድ ባሪያ ወይም ሴት ባሪያ ቢወጋ፥ የበሬው ባለቤት ሠላሳ የብር ሰቅል ለጌታቸው ይስጥ፥ በሬውም ይወገር።

Ver Capítulo



ዘፀአት 21:32
9 Referencias Cruzadas  

የምድያም ነጋዶችም አለፉ፥ እነርሱም ዮሴፍን አንሥተው ከጉድጓድ አወጡት፥ ለእስማኤላውያንም ዮሴፍን በሃያ ብር ሸጡት፥ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብጽ ወሰዱት።


ወንድን ልጅ ቢወጋ ወይም ሴትን ልጅ ቢወጋ፥ ይህንኑ ፍርድ ያድርጉበት።


አንድ ሰው ጉድጓድ ቢከፍት፥ ወይም ጉድጓድ ቢቆፍር ሳይከድነው ቢቀርና በሬ ወይም አህያ ቢወድቅበት፥


በዓናቶትም ያለውን እርሻ ከአጐቴ ልጅ ከአናምኤል ገዛሁ፥ ዐሥራ ሰባት ሰቅል ብርም መዘንሁለት።


እንዲህ አላቸው “አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፥ ምን ትሰጡኛላችሁ?” እነርሱም ሠላሳ ብር መዘኑለት።


ነገር ግን እንደ ሰው ሆኖ በመወለድ የባርያን መልክ ይዞ ራሱን ባዶ አደረገ፤ በሰው አምሳል ተገኝቶ፥