ዘፀአት 21:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በሬ ወንድን ወይም ሴትን እስኪሞቱ ድረስ ቢወጋ፥ በሬው ይወገር፥ ሥጋውም አይበላ፤ የበሬው ባለቤት ግን ንጹሕ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በሬ አንድን ወንድ ወይም ሴት ወግቶ ቢገድል፣ በሬው በድንጋይ ተወግሮ ይሙት፤ ሥጋውም አይበላ፤ ነገር ግን የበሬው ባለቤት በኀላፊነት አይጠየቅም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በሬ ሰው ወግቶ ቢገድል በድንጋይ ተወግሮ ይሙት፤ ሥጋውም አይበላ፤ ባለ ንብረቱም በነጻ ይለቀቅ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በሬም ወንድን ወይም ሴትን ቢወጋ ቢሞቱም፥ በሬው በድንጋይ ይወገር፤ ሥጋውም አይበላ፤ የበሬው ባለቤት ግን ንጹሕ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሬም ወንድን ወይም ሴትን እስኪሞቱ ድረስ ቢወጋ፥ በሬው ይወገር፥ ሥጋውም አይበላ፤ የበሬው ባለቤት ግን ንጹሕ ነው። |
ነገር ግን በሬው አስቀድሞ ተዋጊ ቢሆን፥ ለባለቤቱ አስጠንቅቀውት ባይጠብቀውና ወንድን ወይም ሴትን ቢገድል፥ በሬው ይወገር፥ ባለቤቱ ደግሞ ይገደል።