ዘፀአት 2:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የፈርዖንም ልጅ፦ “ሂጂ” አለቻት፤ ብላቴናይቱም ሄዳ የሕፃኑን እናት ጠራች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የፈርዖንም ልጅ፣ “መልካም፣ ሂጂ” አለቻት። ልጅቱም ሄዳ የሕፃኑን እናት ይዛ መጣች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አዎ፥ ሄደሽ ጥሪልኝ” ስላለቻት ልጅቱ ሄደች፤ የሕፃኑንም እናት ጠርታ አመጣች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የፈርዖንም ልጅ፥ “ሂጂና ጥሪልኝ” አለቻት፤ ብላቴናዪቱም ሄዳ የሕፃኑን እናት ጠራች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የፈርዖንም ልጅ፦ “ሂጂ” አለቻት፤ ብላቴናይቱም ሄዳ የሕፃኑን እናት ጠራች። |
በአንቺ በኩል አለፍሁ፥ አየሁሽም፥ እነሆ ጊዜሽ የፍቅር ጊዜ ነበር፥ እኔም መጐናጸፊያዬን በላይሽ ላይ ዘረጋሁና ዕርቃንሽን ሸፈንሁ፥ ማልሁልሽም ከአንቺም ጋር ቃል ኪዳን ገባሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ አንቺም የእኔ ሆንሽ።