La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 2:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የፈርዖንም ልጅ ልትታጠብ ወደ ወንዝ ወረደች፤ ደንገጥሮችዋም በወንዝ ዳር ይሄዱ ነበር፤ ሣጥኑንም በቄጠማ ውስጥ አየች፥ ደንገጥሩዋንም ልካ አስመጣችው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚህ ጊዜ የፈርዖን ልጅ ልትታጠብ ወደ አባይ ወንዝ ወረደች፤ በምትታጠብበትም ጊዜ ደንገጥሮቿ በወንዙ ዳር ወዲያና ወዲህ ይሉ ነበር፤ በቄጠማውም መካከል የተቀመጠ ቅርጫት አይታ ከደንገጥሮቿ አንዷን እንድታመጣው ላከቻት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚህ ጊዜ የንጉሡ ሴት ልጅ ልትታጠብ ወደ ወንዝ ወረደች፤ ሴቶች አገልጋዮችዋም በወንዙ ዳር ይሄዱ ነበር፤ እርስዋም በቀጤማ መካከል የተቀመጠ አንድ ቅርጫት አየች፤ አገልጋይዋንም ልካ አስመጣችው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የፈ​ር​ዖ​ንም ሴት ልጅ ልት​ታ​ጠብ ወደ ወንዝ ወረ​ደች፤ ደን​ገ​ጥ​ሮ​ች​ዋም በወ​ንዝ ዳር ይሄዱ ነበር፤ ሣጥ​ኑ​ንም በቄ​ጠማ ውስጥ አየች፤ ደን​ገ​ጥ​ር​ዋ​ንም ልካ አስ​መ​ጣ​ችው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የፈርዖንም ልጅ ልትታጠብ ወደ ወንዝ ወረደች፤ ደንገጥሮችዋም በወንዝ ዳር ይሄዱ ነበር፤ ሣጥኑንም በቄጠማ ውስጥ አየች፤ ደንገጥሩዋንም ልካ አስመጣችው።

Ver Capítulo



ዘፀአት 2:5
12 Referencias Cruzadas  

ከወንዙም ውሃ ጠጣ፤ ቁራዎችም ዘወትር ጧትና ማታ እንጀራና ሥጋ ያመጡለት ነበር።


ምላሳችንን እናበረታለን፥ ከንፈራችን የእኛ ነው፥ ጌታችን ማን ነው? የሚሉትን።


ለመዘምራን አለቃ፥ ስለ ምሥጢር፥ የቆሬ ልጆች መዝሙር።


የምድር ትሑታንን ያድን ዘንድ እግዚአብሔር ለፍርድ በተነሣ ጊዜ።


እርሱም ዓለምን በጽድቅ ይፈርዳታል፥ አሕዛብንም በቅንነት ይዳኛቸዋል።


በከፈተችውም ጊዜ ሕፃኑን አየች፥ እነሆም ሕፃኑ ያለቅስ ነበር፤ አዘነችለትም፦ “ይህ ከዕብራውያን ልጆች አንዱ ነው” አለች።


ወደ ፈርዖን በጠዋት ሂድ፤ እነሆ ወደ ውኃ ይወጣል፥ አንተም እንድትገናኘው በወንዝ ዳር ትቆማለህ፤ ወደ እባብም የተለወጠውን በትር በእጅህ ትወስዳለህ።


ጌታም እንዲሁ አደረገ፤ በፈርዖን ቤት፥ በአገልጋዮቹም ቤቶች ውስጥ ብዙ የዝንብ መንጋ መጣ፤ በግብጽም ምድር ሁሉ ላይ፤ ከዝንቡ መንጋ የተነሣ ምድር ተበላሸች።


የንጉሥ ልብ እንደ ውኃ ፈሳሾች በጌታ እጅ ነው፥ ወደ ወደደውም ያዘነብለዋል።


እኔ ግን ከምስጋና ቃል ጋር እሠዋልሃለሁ፤ የተሳልሁትንም እፈፅማለሁ። ደኅንነት ከጌታ ነውና።”


በተጣለም ጊዜ የፈርዖን ልጅ አነሣችው፤ ልጅም ይሆናት ዘንድ አሳደገችው።