Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 2:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 በከፈተችውም ጊዜ ሕፃኑን አየች፥ እነሆም ሕፃኑ ያለቅስ ነበር፤ አዘነችለትም፦ “ይህ ከዕብራውያን ልጆች አንዱ ነው” አለች።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ቅርጫቱን ስትከፍተው ሕፃኑን በውስጡ አየች፤ ያለቅስ ስለ ነበርም ዐዘነችለትና፣ “ከዕብራውያን ሕፃናት አንዱ መሆን አለበት” አለች።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 በከፈተችውም ጊዜ አንድ ሕፃን በውስጡ አገኘች፤ ሕፃኑም ያለቅስ ስለ ነበር አዘነችለትና “ይህ ከዕብራውያን ሕፃናት አንዱ ነው” አለች።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ሣጥ​ኑን በከ​ፈ​ተ​ችም ጊዜ ሕፃ​ኑን አየች፤ እነ​ሆም፥ ሕፃኑ በሣ​ጥኑ ውስጥ ያለ​ቅስ ነበር፤ የፈ​ር​ዖ​ንም ልጅ አዘ​ነ​ች​ለት፥ “ይህ ሕፃን ከዕ​ብ​ራ​ው​ያን ልጆች አንዱ ነው” አለች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 በከፈተችውም ጊዜ ሕፃኑን አየች፤ እነሆም ሕፃኑ ያለቅስ ነበር፤ አዘነችለትም፤ “ይህ ከዕብራውያን ልጆች አንድ ነው፤” አለች።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 2:6
10 Referencias Cruzadas  

ኃጢአታቸውንና አንተን ያሳዘኑበትን ዐመፅ ሁሉ ይቅር በል፤ ጠላቶቻቸውም እንዲራሩላቸው አድርግ፤


ጌታ ሆይ፥ ጆሮህ የባርያህን ጸሎት፥ ስምህን በመፍራት የሚደሰቱትን የባርያዎችህን ጸሎት ያድምጥ፤ ዛሬ ለባርያህ እባክህን አከናውንለት፥ በዚህም ሰው ፊት ሞገስን ስጠው። እኔም የንጉሡ ጠጅ አሳላፊ ነበርኩ።


በማረኩአቸውም ሁሉ ፊት ሞገስን ሰጣቸው።


ፈርዖንም፦ “የሚወለደውን ወንድ ልጅ ሁሉ ወደ ዓባይ ወንዝ ጣሉት፥ ሴትን ልጅ ሁሉ ግን በሕይወት እንድትኖር ተዉአት” ብሎ ሕዝቡን ሁሉ አዘዘ።


የፈርዖንም ልጅ ልትታጠብ ወደ ወንዝ ወረደች፤ ደንገጥሮችዋም በወንዝ ዳር ይሄዱ ነበር፤ ሣጥኑንም በቄጠማ ውስጥ አየች፥ ደንገጥሩዋንም ልካ አስመጣችው።


እኅቱም ለፈርዖን ልጅ፦ “ሕፃኑን እንድታጠባልሽ ሄጄ የምታጠባ ሴት ከዕብራውያን ሴቶች ልጥራልሽን?” አለቻት፤


የንጉሥ ልብ እንደ ውኃ ፈሳሾች በጌታ እጅ ነው፥ ወደ ወደደውም ያዘነብለዋል።


አዋጁም፦ ሰው ሁሉ ዕብራዊ የሆነውን ወንድ ባርያውንና ዕብራዊት የሆነችውን ሴት ባርያውን አርነት እንዲያወጣ፥ አይሁዳዊ ወንድሙንም ማንም እንዳይገዛ የሚል ነው።


በተጣለም ጊዜ የፈርዖን ልጅ አነሣችው፤ ልጅም ይሆናት ዘንድ አሳደገችው።


በመጨረሻም ሁላችሁ በአንድ ልብ ሁኑ፤ እርስ በእርሳችሁ ተሳሰቡ፤ በወንድማማችነት ፍቅር ተዋደዱ፤ ርኅሩኆችና ትሑታን ሁኑ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos