ዘፀአት 18:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም ሁለቱን ልጆቿን ጭምር። የአንደኛው ስም ጌርሾም ነበረ “በባዕድ አገር መጻተኛ ነኝ” ብሏልና፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴ፣ “በባዕድ አገር መጻተኛ ነኝ” ለማለት የመጀመሪያ ልጁን ስም ጌርሳም አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ከሙሴ የተወለዱትን ሁለቱን ልጆችዋን ይዞለት መጣ፤ ሙሴ “በባዕድ አገር መጻተኛ ነኝ” በማለት የመጀመሪያ ልጁን ጌርሾም ብሎ ጠራው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአንደኛው ስም ጌርሳም ነበረ፤ አባቱ “በሌላ ሀገር ስደተኛ ነበርሁ” ብሎአልና፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱ የአንደኛው ስም ጌርሳም ነበረ፤ አባቱ፦ በሌላ አገር ስደተኛ ነበርሁ ብሎአልና፤ |
እነዚህ ሁሉ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል ሳያገኙ እምነታቸውን እንደ ጠበቁ ሞቱ፤ ሆኖም ከርቀት አይተውት ሰላምታ አቀረቡለት፤ በዚህ ምድር ሲኖሩም እንግዶችና መጻተኞች ለመሆንም ታመኑ።
እዚያም የዳን ሰዎች ለራሳቸው ጣዖታት አቆሙ፤ የሙሴ ልጅ፥ የጌርሳም ልጅ ዮናታንና የእርሱም ልጆች ምድሪቱ እስከ ተማረከችበት ጊዜ ድረስ ለዳን ነገድ ካህናት ሆኗቸው፤