Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 18:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እንዲሁም ከሙሴ የተወለዱትን ሁለቱን ልጆችዋን ይዞለት መጣ፤ ሙሴ “በባዕድ አገር መጻተኛ ነኝ” በማለት የመጀመሪያ ልጁን ጌርሾም ብሎ ጠራው፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ሙሴ፣ “በባዕድ አገር መጻተኛ ነኝ” ለማለት የመጀመሪያ ልጁን ስም ጌርሳም አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እንዲሁም ሁለቱን ልጆቿን ጭምር። የአንደኛው ስም ጌርሾም ነበረ “በባዕድ አገር መጻተኛ ነኝ” ብሏልና፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የአ​ን​ደ​ኛው ስም ጌር​ሳም ነበረ፤ አባቱ “በሌላ ሀገር ስደ​ተኛ ነበ​ርሁ” ብሎ​አ​ልና፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ከእነርሱ የአንደኛው ስም ጌርሳም ነበረ፤ አባቱ፦ በሌላ አገር ስደተኛ ነበርሁ ብሎአልና፤

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 18:3
8 Referencias Cruzadas  

ሙሴም ጌርሾምና ኤሊዔዘር ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩት፤


እግዚአብሔር ሆይ! ጸሎቴን ስማ፤ ጩኸቴንም አድምጥ፤ ሳለቅስም ቶሎ ብለህ እርዳኝ፤ እኔ ለጥቂት ጊዜ የአንተ እንግዳ ነኝ፤ እንደ ቀድሞ አባቶቼም በስደተኛነት የምኖር ነኝ።


እርስዋም ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ ሙሴም “እኔ በዚህ ምድር መጻተኛ ነኝ” ሲል ልጁን ጌርሾም ብሎ ጠራው።


ስለዚህም ሙሴ ሚስቱንና ወንዶች ልጆቹን በአህያ ላይ አስቀምጦ ወደ ግብጽ መጓዝ ጀመረ፤ ተአምራት የሚገለጥበት የእግዚአብሔርንም በትር በእጁ ይዞ ነበር።


ሙሴ ይህን በሰማ ጊዜ ከግብጽ አገር ሸሽቶ ወደ ምድያም አገር ሄደና እዚያ በስደት ኖረ፤ በዚያ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ።


እነዚህ ሁሉ በእምነት እንዳሉ ሞቱ፤ እግዚአብሔር ሊሰጣቸው ቃል የገባላቸውንም ነገር አላገኙም፤ ነገር ግን ከሩቅ አይተው ልክ እንዳገኙት አድርገው በደስታ ተቀበሉት። በምድር ላይ እንግዶችና መጻተኞች መሆናቸውንም ተገነዘቡ።


ወዳጆች ሆይ፥ በዚህ ዓለም እንግዶችና መጻተኞች ስለ ሆናችሁ ከነፍስ ጋር ከሚዋጉት ከሥጋ ፍትወቶች እንድትርቁ ዐደራ እላችኋለሁ።


የዳን ሰዎችም ያመልኩት ዘንድ ያን ጣዖት በዚያ አኖሩ፤ ከሙሴ ልጅ ከጌርሾም የተወለደው ዮናታንም ለዳን ነገድ ካህን ሆኖ ማገልገል ጀመረ። የእርሱም ዘሮች ሕዝቡ ተማርከው እስከ ተሰደዱበት ጊዜ ድረስ ማገልገላቸውን ቀጠሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos