ዘፀአት 18:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይትሮም እንዲህ አለ፦ “ከግብጽ እጅና ከፈርዖን እጅ ያዳናችሁ፥ ከግብጽም እጅ በታች ሕዝቡን ያዳነ ጌታ ይባረክ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም አለ፤ “ከግብጻውያን እጅና ከፈርዖን ለታደጋችሁ፣ ከግብጻውያን እጅ ሕዝቡን ለታደገ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህም አለ፥ “ከግብጽ ንጉሥና ከሕዝቡም እጅ ያዳናችሁ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን! ሕዝቡንም ከባርነት ነጻ ያወጣ እግዚአብሔር ይመስገን! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮቶርም፥ “ከግብፃውያን እጅና ከፈርዖን እጅ ሕዝቡን የአዳነ እግዚአብሔር ቡሩክ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮቶርም፦ ከግብፃውያንና ከፈርዖን እጅ ያዳናችሁ፥ ከግብፃውያንም እጅ ሕዝቡን ያዳነ እግዚአብሔር ይባረክ። |
እንዲህም አለ፦ “ቸርነቱንና እውነቱን ከጌታዬ ያላራቀ የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፥ እኔ በመንገድ ሳለሁ እግዚአብሔር ወደ ጌታዬ ወንድሞች ቤት መራኝ።”
አሒማዓጽም ጮኾ ንጉሡን፥ “ሁሉም ደህና ሆኖአል” አለ፤ ከዚያም ወደ መሬት ለጥ ብሎ በንጉሡ ፊት እጅ ነሣና፥ “በጌታዬ በንጉሡ ላይ እጃቸውን ያነሡትን ሰዎች አሳልፎ የሰጠ ጌታ አምላክህ የተመሰገነ ይሁን!” አለ።
እንዲህም አላቸው፤ “የእስራኤል አምላክ ጌታ ይባረክ! ለአባቴ ለዳዊት የገባውን ቃል ኪዳን በአፉ እንደ ተናገረ፥ በእጁም ፈጽሙአል፤ እርሱም እንዲህ የሚል ነው፦
“በገባው የተስፋ ቃል መሠረት ለሕዝቡ ሰላምን የሰጠ እግዚአብሔር ይመስገን፤ በአገልጋዩ በሙሴ አማካይነት ከሰጠውም መልካም ተስፋ ምንም የቀረ የለም።
ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ሕያው የሆነውን ተስፋ የሰጠን፥ ከምሕረቱ ብዛት በአዲስ ልደት ልጆቹ ያደረገን፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እና አባት ይመስገን፤
እርሱም ቄናውያንን፥ “ከእነርሱ ጋር እንዳላጠፋችሁ ከአማሌቃውያን ራቁ፤ ተለዩአቸውም፤ ምክንያቱም እናንተ እስራኤላውያን ከግብጽ ምድር በወጡ ጊዜ ቸርነት አድርጋችሁላቸዋልና” አላቸው። ስለዚህ ቄናውያን ከአማሌቃውያን ተለዩ።