ዘፀአት 17:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱም ሙሴ እንዳለው አደረገ፥ ከአማሌቅም ጋር ተዋጋ፤ ሙሴ፥ አሮንና ሑር ወደ ኮረብታው ጫፍ ወጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ኢያሱ ሙሴ ባዘዘው መሠረት ከአማሌቃውያን ጋራ ተዋጋ፤ ሙሴ፣ አሮንና ሖርም ወደ ኰረብታው ጫፍ ወጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢያሱም የሙሴን ትእዛዝ በመፈጸም ዐማሌቃውያንን ለመውጋት ወጣ፤ ሙሴ፥ አሮንና ሑር ወደ ኮረብታው ጫፍ ወጡ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም ሙሴ እንደ አለው አደረገ፤ ወጥቶም ከዐማሌቅ ጋር ተዋጋ፤ ሙሴና አሮን፥ ሖርም ወደ ኮረብታው ራስ ወጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱም ሙሴ እንዳለው አደረገ፥ ከአማሌቅም ጋር ተዋጋ፤ ሙሴና አሮንም ሖርም ወደ ኮረብታው ራስ ወጡ። |
የሙሴ እጆች ግን ዝለው ነበር፤ ድንጋይም ወሰዱ፥ በበታቹም አኖሩ፥ እርሱም ተቀመጠበት፤ አሮንና ሑርም አንዱ በዚህ አንዱ በዚያ ሆነው እጆቹን ያዙ፤ ፀሐይም እስክትገባ ድረስ እጆቹ ቀጥ አሉ።
ሽማግሌዎቹንም፦ “ወደ እናንተ እስክንመለስ ድረስ በዚህ ቆዩን፤ አሮንና ሑርም እነሆ ከእናንተ ጋር ናቸው፥ ባለ ጉዳይም ቢኖር ወደ እነርሱ ይምጣ” አላቸው።