የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር እንደ ወጡ፥ ጌታ ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን በገባ ጊዜ፥ ሙሴ በኮሬብ ተራራ በቃል ኪዳኑ ታቦት ውስጥ ካኖራቸው ከሁለቱ የድንጋይ ጽላቶች በቀር ሌላ ምንም ነገር አልነበረም።
ዘፀአት 16:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ ተጠብቆ እንዲኖር አሮን በምስክሩ ፊት አስቀምጠው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው አሮን፣ መናው ይጠበቅ ዘንድ በምስክሩ ፊት አስቀመጠው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት አሮን ለመጪው ትውልድ ተጠብቆ እንዲኖር መናውን በኪዳኑ ታቦት ፊት አኖረው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ ይጠበቅ ዘንድ አሮን በምስክሩ ፊት አኖረው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ ይጠበቅ ዘንድ አሮን በምስክሩ ፊት አኖረው። |
የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር እንደ ወጡ፥ ጌታ ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን በገባ ጊዜ፥ ሙሴ በኮሬብ ተራራ በቃል ኪዳኑ ታቦት ውስጥ ካኖራቸው ከሁለቱ የድንጋይ ጽላቶች በቀር ሌላ ምንም ነገር አልነበረም።
ከመጋረጃው ውጭ ባለው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ታቦት ፊት አሮንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በጌታ ፊት ያሰናዱት፤ በእስራኤል ልጆች ዘንድ በትውልዳቸው የዘለዓለም ሥርዓት ይሁን።”
ከእርሱም ጥቂት ትወቅጣለህ፥ ታደቀዋለህም፥ ከእርሱም ወስደህ አንተን በምገናኝበት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ፊት ታኖረዋለህ። ለእናንተም ፍጹም ቅዱስ ይሆንላችኋል።
በሙሴ ትእዛዝ መሠረት የሌዋውያን አገልግሎት ሊሆን በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታማር እጅ የተቆጠረው የማደሪያው፥ የምስክሩ ማደሪያ፥ ዕቃ ድምር ይህ ነው።
ነገር ግን በምስክሩ ማደሪያና በዕቃው ሁሉ የእርሱም በሆነው ነገር ሁሉ ላይ ሌዋውያንን ሹማቸው። ማደሪያውንና ዕቃዎቹን ሁሉ ይሸከሙ፥ ያገልግሉትም፥ በማደሪያውም ዙሪያ ይስፈሩ።
ነገር ግን በእስራኤል ልጆች ጉባኤ ላይ ቁጣ እንዳይወርድ ሌዋውያን በምስክሩ ማደሪያ ዙሪያ ይስፈሩ፤ ሌዋውያንም የምስክሩን ማደሪያ ይጠብቁ።”
ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የአሮንን በትር ወደ ምስክሩ ፊት መልሰህ አኑር፤ እርሱም ለሚያምፁብኝ ልጆች ምልክት ሆኖ ይቀመጥ፤ እነርሱም እንዳይሞቱ በእኔ ላይ ማጉረምረማቸውን ታስቆምበታለህ።”