በኢየሩሳሌምም ተገኝተው የነበሩ የእስራኤል ልጆች የቂጣውን በዓል በታላቅ ደስታ ሰባት ቀን አከበሩ፤ ሌዋውያኑና ካህናቱም በዜማ ዕቃ ለጌታ እየዘመሩ ዕለት ዕለት ጌታን ያመሰግኑ ነበር።
ዘፀአት 13:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰባት ቀን ያልቦካ ቂጣ ትበላለህ፥ በሰባተኛውም ቀን ለጌታ በዓል ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሰባት ቀን ያለ እርሾ የተጋገረ ቂጣ ትበላላችሁ፤ በሰባተኛውም ቀን ለእግዚአብሔር በዓል ታደርጋላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰባት ቀን ሙሉ እርሾ የሌለበት ቂጣ ትበላላችሁ፤ በሰባተኛውም ቀን ለእግዚአብሔር ክብር በዓል ታደርጋላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስድስት ቀን ቂጣ ትበላላችሁ፤ ሰባተኛውም ቀን የእግዚአብሔር በዓል ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰባት ቀን ቂጣ እንጀራ ትበላለህ፤ በሰባተኛውም ቀን ለእግዚአብሔር በዓል ይሆናል። |
በኢየሩሳሌምም ተገኝተው የነበሩ የእስራኤል ልጆች የቂጣውን በዓል በታላቅ ደስታ ሰባት ቀን አከበሩ፤ ሌዋውያኑና ካህናቱም በዜማ ዕቃ ለጌታ እየዘመሩ ዕለት ዕለት ጌታን ያመሰግኑ ነበር።