ዘፀአት 12:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዳላችሁትም መንጎቻችሁንና ከብቶቻችሁን ውሰዱ፥ ሂዱም፥ እኔንም ደግሞ ባርኩኝ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዳላችሁት የበግና የፍየል መንጋችሁን፣ የቀንድና የጋማ ከብቶቻችሁን ይዛችሁ ሂዱ፤ እኔንም ባርኩኝ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የበግ፥ የፍየልና የቀንድ ከብት መንጋችሁን ሁሉ ይዛችሁ ሂዱ፤ እኔንም ባርኩኝ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጎቻችሁንም፥ ላሞቻችሁንም ውሰዱ፤ ሂዱም፤ እኔንም ደግሞ ባርኩኝ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዳላችሁም መንጎቻችሁንና ከብቶቻችሁን ውሰዱ፤ ሂዱም፤ እኔንም ደግሞ ባርኩኝ” አለ። |
ከብቶቻችን ከእኛ ጋር ይሄዳሉ አንድ ሰኮናም አይቀርም፥ ጌታ አምላካችንን ለማገልገል ከእነርሱ እንወስዳለንና፤ ጌታን የምናገለግለው በምን እንደሆነ እዚያ እስክንደርስ አናውቅም።”
ሙሴም፦ “ወጣቶቻችን፥ ሽማግሌዎቻችን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን፥ በጎቻችንና ከብቶቻችን ከእኛ ጋር ይሄዳሉ የጌታን በዓል እናደርጋለንና” አለ።