ዘፀአት 12:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም ይሆናል፤ ልጆቻችሁ፦ ‘ይህ አገልግሎት ለእናንተ ምንድነው?’ ባሉአችሁ ጊዜ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጆቻችሁ ስለ ሥርዐቱ ምንነት ሲጠይቋችሁ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጆቻችሁ ‘ይህ ሥርዓት ምንድን ነው?’ ብለው በሚጠይቁአችሁ ጊዜ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጆቻችሁ፦ ‘ይህ ሥርዐት ለእናንተ ምንድር ነው?’ ባሉአችሁ ጊዜ እናንተ፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ይሆናል፤ ልጆቻችሁ፥ ‘ይህ አምልኮ ለእናንተ ምንድር ነው?’ |
ይህም በልጅህና በልጅ ልጅህ ጆሮ እንድትነግርና ግብፃውያንን እንዴት እንዳሞኘኋቸው፥ በመካከላቸው ያስቀመጥኩት ምልክቶቼም ጌታ እንደሆንኩ እንድታውቁ ነው።”
“የቀድሞውን ዘመን አስታውስ፤ የብዙ ትውልድንም ዓመታት አስተውል፥ አባትህን ጠይቅ፥ እርሱም ያስታውቅሃል፥ ሽማግሌዎችህን ጠይቅ፥ እነርሱም ይነግሩሃል።