ዘፀአት 11:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንዱ ከጎረቤቱ ሴቲቱም ከጎረቤቷ የብር ዕቃና የወርቅ ዕቃ እንዲጠይቁ በሕዝቡ ጆሮ ተናገር።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለእስራኤል ሕዝብ፣ ለወንዶቹም ሆነ ለሴቶቹ የብርና የወርቅ ዕቃዎች ከየጎረቤቶቻቸው ስጡን ብለው እንዲወስዱ ንገራቸው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሁንም የእስራኤል ሕዝብ ወንዶቹም ሴቶቹም ጐረቤቶቻቸውን ሁሉ የወርቅና የብር ጌጣጌጥ እንዲሰጡአቸው ይጠይቁ ዘንድ ንገራቸው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንዱ ከወዳጁ፥ ሴቲቱም ከወዳጅዋ የብርና የወርቅ ዕቃ፥ ልብስም ይዋሱ ዘንድ በሕዝቡ ጆሮ በስውር ተናገር።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንዱ ከወዳጁ ሴቲቱም ከወዳጅዋ የብርና የወርቅ ዕቃ ይሹ ዘንድ በሕዝቡ ጆሮ ተናገር አለው።” |
ነገር ግን እያንዳንዲቱ ሴት ከጎረቤትዋ በቤትዋም ካለችው ሴት የብር እቃ የወርቅ እቃ ልብስም ትለምናለች፤ በወንዶችና በሴቶች ልጆቻችሁ ላይ ታደርጉታላችሁ፤ ግብፃውያንንም ትበዘብዛላችሁ።”
ልባቸው የተነሣሣ ወንዶችና ሴቶች ሁሉ የአፍንጫ ጌጦችን፥ ሎቲዎችን፥ ቀለበቶችን፥ ድሪዎችን፥ የወርቅ ጌጦችን ሁሉ አመጡ፤ ሰዎች ሁሉ የወርቅ ስጦታ ለጌታ አመጡ።