አሁንም ሕዝቅያስ አያስታችሁ፥ እንዲህም አያባብላችሁ፥ አትመኑትም፤ ከአሕዛብና ከመንግሥታት አማልክት ሁሉ ሕዝቡን ከእጄና ከአባቶቼ እጅ ለማዳን ማንም አልቻለም፤ ይልቁንስ አምላካችሁ ከእጄ ሊያድናቸሁ እንዴት ይችላል?’ ”
ዘፀአት 10:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እሱም እንዲህ አላቸው፦ “ጌታ ከእናንተ ጋር ይሁን እናንተንና ልጆቻችሁን እለቅቃለሁ፥ ነገር ግን ክፉ ነገር በፊታችሁ እንደሚሆን ተመልከቱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈርዖንም እንዲህ አለ፤ “ከሴቶቻችሁና ከልጆቻችሁ ጋራ እንድትሄዱ እለቅቃችኋለሁ፤ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋራ ይሁን፤ ነገር ግን ተንኰል ዐስባችኋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡም እንዲህ አለ፦ “እስቲ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን፤ የዐመፅ ሤራ ማቀዳችሁ ግልጥ ስለ ሆነ ሴቶቻችሁንና ልጆቻችሁን ይዛችሁ እንድትሄዱ አልፈቅድላችሁም! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈርዖንም አላቸው፥ “እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን፤ እነሆ፥ እናንተን ስለቅ ልጆቻችሁንም መልቀቅ አለብኝን? ክፉ ነገር እንደሚገጥማችሁ ዕወቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈርዖንም፦ “እናንተን ከልጆቻችሁ ጋር ስለቅቅ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን፤ ነገር ግን ክፉ ነገር በአእምሮአችሁ እንዳለ እወቁ። |
አሁንም ሕዝቅያስ አያስታችሁ፥ እንዲህም አያባብላችሁ፥ አትመኑትም፤ ከአሕዛብና ከመንግሥታት አማልክት ሁሉ ሕዝቡን ከእጄና ከአባቶቼ እጅ ለማዳን ማንም አልቻለም፤ ይልቁንስ አምላካችሁ ከእጄ ሊያድናቸሁ እንዴት ይችላል?’ ”
ሙሴም፦ “ወጣቶቻችን፥ ሽማግሌዎቻችን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን፥ በጎቻችንና ከብቶቻችን ከእኛ ጋር ይሄዳሉ የጌታን በዓል እናደርጋለንና” አለ።