ዘፀአት 1:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አዋላጆቹ ግን እግዚአብሔርን ፈሩ፥ የግብጽ ንጉሥም እንዳዘዛቸው አላደረጉም፥ ወንዶቹን ሕፃናትንም በሕይወት ይኖሩ ዘንድ ተዋቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አዋላጆቹ ግን እግዚአብሔርን ስለ ፈሩ የግብጽ ንጉሥ ያዘዛቸውን አልፈጸሙም፤ ወንዶቹንም ልጆች በሕይወት እንዲኖሩ ተዉአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አዋላጆቹ ግን እግዚአብሔርን በመፍራት የግብጽ ንጉሥ እንዳዘዛቸው አላደረጉም፤ ወንዶችንም ልጆች በሕይወት እንዲኖሩ ተዉአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አዋላጆች ግን እግዚአብሔርን ፈሩ፤ የግብፅ ንጉሥም እንደ አዘዛቸው አላደረጉም፤ ወንዶቹን ሕፃናትንም አዳኑአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አዋላጆች ግን እግዚአብሔርን ፈሩ፤ የግብፅ ንጉሥም እንዳዘዛቸው አላደረጉም፤ ወንዶቹን ሕፃናትንም አዳኑአቸው። |
ከእኔ በፊት የነበሩት የቀድሞ ገዢዎች ግን በሕዝቡ ላይ አክብደውባቸው ነበር፥ ምግብ፥ ወይና አርባ ሰቅል ብር ከእነሱ ይወስዱ ነበር፤ አገልጋዮቻቸው ደግሞ ሕዝቡን ይጨቁኑአቸው ነበር፤ እኔ ግን እግዚአብሔርን ስለ ፈራሁ እንዲህ አላደረግሁም።
የዖምሪን ሥርዓትና የአክዓብን ቤት ሥራ ሁሉ ጠብቀሃልና፥ በምክራቸውም ሄዳችኋልና፤ ስለዚህ አንተን ለጥፋት ነዋሪዎቿን ደግሞ ለመዘባበቻ ሰጥቻችኋለሁ፥ የሕዝቤንም ስድብ ትሸከማላችሁ።
ከዚያም ንጉሡ በአጠገቡ የቆሙትን ዘቦች፥ “እነዚህም የጌታ ካህናት ከዳዊት ጋር ስላበሩ፥ ዳዊት መኰብለሉንም እያወቁ ስላልነገሩኝ ዞራችሁ ግደሏቸው” ሲል አዘዛቸው። የንጉሡ አገልጋዮች ግን እጃቸውን አንሥተው የጌታን ካህናት ለመምታት ፈቃደኞች አልሆኑም።