ጳውሎስና በርናባስም ገልጠው “የእግዚአብሔር ቃል አስቀድሞ ለእናንተ ይነገር ዘንድ ያስፈልጋል፤ ከገፋችሁትና የዘለዓለም ሕይወት እንዳይገባችሁ በራሳችሁ ከፈረዳችሁ ግን፥ እነሆ፥ ወደ አሕዛብ ዘወር እንላለን።
ኤፌሶን 6:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቃል እንዲሰጠኝና አፌን በመክፈት የወንጌልን ምሥጢር በግልጥ እንዳስታውቅ፥ ስለ እኔም ለምኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የወንጌልን ምስጢር ለመግለጥ አፌን በምከፍትበት ጊዜ ሁሉ በድፍረት እንድናገር ቃል ይሰጠኝ ዘንድ ጸልዩልኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የወንጌልን ምሥጢር ያለ ፍርሀት እንድገልጥ በምናገርበት ጊዜ አስፈላጊውን ቃል እንዲሰጠኝ ለእኔም ጸልዩልኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእኔም፦ ቃልን እንዲሰጠኝ፥ አፌንም ከፍቼ የወንጌልን ምሥጢር በግልጥ እንድናገር ጸልዩልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞ የወንጌልን ምሥጢር በግልጥ እንዳስታውቅ አፌን በመክፈት ቃል ይሰጠኝ ዘንድ ስለ እኔ ለምኑ፤ |
ጳውሎስና በርናባስም ገልጠው “የእግዚአብሔር ቃል አስቀድሞ ለእናንተ ይነገር ዘንድ ያስፈልጋል፤ ከገፋችሁትና የዘለዓለም ሕይወት እንዳይገባችሁ በራሳችሁ ከፈረዳችሁ ግን፥ እነሆ፥ ወደ አሕዛብ ዘወር እንላለን።
ጴጥሮስና ዮሐንስም በግልጥ እንደ ተናገሩ ባዩ ጊዜ፥ መጽሐፍን የማያውቁና ያልተማሩ ሰዎች እንደ ሆኑ አስተውለው አደነቁ፤ ከኢየሱስም ጋር እንደ ነበሩ አወቁአቸው፤
አሁንም፥ ጌታ ሆይ! ወደ ዛቻቸው ተመልከት፤ ለመፈወስም እጅህን ስትዘረጋ በቅዱስ ብላቴናህም በኢየሱስ ስም ምልክትና ድንቅ ሲደረግ፥ ባርያዎችህ በፍጹም ግልጥነት ቃልህን እንዲናገሩ ስጣቸው።”
በርናባስ ግን ወስዶ ወደ ሐዋርያት አገባውና ጌታን በመንገድ እንዴት እንዳየውና እንደ ተናገረው በደማስቆም በኢየሱስ ስም ደፍሮ እንዴት እንደ ነገረተረከላቸው።
ነገር ግን፥ እግዚአብሔር አስቀድሞ ከዘመናት በፊት ለክብራችን የወሰነውን፥ የእግዚአብሔርን ጥበብ በምሥጢር ተሰውሮም የነበረውን እንናገራለን።
ስለ እናንተ እምነቴ ታላቅ ነው፤ በእናንተ ምክንያት ትምክህቴ ታላቅ ነው፤ እኔም በመጽናናት ተሞልቻለሁ፤ በመከራችን ሁሉ ደስታዬ ወሰን የለውም።
ነገር ግን በነገር ሁሉ፥ በእምነት፥ በቃል፥ በእውቀት፥ በትጋት፥ እንዲሁም ለእኛ በፍቅራችሁ ልቃችሁ እንደተገኛችሁ፥ በዚህ ቸር ሥራ ደግሞ ልቃችሁ ተገኙ።
እንዲህም የምጋደለው ልባቸው እንዲጽናና፥ በፍቅርም በአንድነት እንዲተሳሰሩ፥ በፍጹም ማስተዋልም የሚገኘውን ባለጠግነት ሁሉ እንዲኖራቸው፥ የእግዚአብሔርንም ምሥጢር እርሱንም ክርስቶስን እንዲያውቁ ነው፤
ነገር ግን እንደምታውቁት በፊልጵስዩስ አስቀድመን መከራንና እንግልትን ብንቀበልም እንኳ፥ በታላቅም ተቃውሞ ፊት የእግዚአብሔርን የምሥራች ቃል ለእናንተ ለመናገር በአምላካችን ድፍረትን አገኘን።
የሃይማኖታችን ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ እርሱም፦ በሥጋ ተገለጠ፥ በመንፈስ ጸደቀ፥ ለመላእክት ታየ፥ በአሕዛብ መካከል ተሰበከ፥ በመላው ዓለም ታመነ፥ በክብር ዐረገ፥ የሚል ነው።