መክብብ 6:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰው ድካም ሁሉ ለአፉ ነው፥ ነፍሱ ግን አትጠግብም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰው ጥረት ሁሉ ለአፉ ነው፤ ፍላጎቱ ግን ፈጽሞ አይረካም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰው በሥራ መድከሙ የሚበላውን ነገር ለማግኘት ነበር፤ ይሁን እንጂ “በቃኝ!” ማለት አያውቅም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰው ድካም ሁሉ በአፉ ነው፥ ነፍሱ ግን አትጠግብም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰው ድካም ሁሉ ለአፉ ነው፥ ነፍሱ ግን አትጠግብም። |
ሰው መቶ ልጆች ቢወልድ፥ እጅግ ዘመንም በሕይወት ቢኖር፥ ዕድሜውም እጅግ ዓመት ቢሆን፥ ነገር ግን ነፍሱ መልካምን ነገር ባትጠግብ፥ መቃብርንም ባያገኝ፥ ከእርሱ ይልቅ ጭንጋፍ ይሻላል አልሁ።
ስለዚህ እላችኋለሁ፤ ስለ ነፍሳችሁ ምን እንደምትበሉና ምን እንደምትጠጡ፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ ምን እንደምትለብሱ አትጨነቁ፤ ነፍስ ከምግብ ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?
ለሚጠፋ መብል አትሥሩ፤ ነገር ግን የለዘለዓለም ሕይወት ለሚሆነው መብል ሥሩ፤ ይህም የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ነው፤ እርሱን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና።”