መክብብ 10:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰነፍ ሥራ ያደክመዋል ወደ ከተማ መሄድ አያውቅምና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሞኝ ሥራ ራሱን ያደክመዋል፤ ወደ ከተማ የሚወስደውንም መንገድ አያውቅም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዕውቀት የጐደለው ሞኝ ሰው ወደ ከተማ መውጣት ስለሚሳነው በሥራው ይደክማል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰነፍ ድካሙ ያሠቃየዋል፥ ወደ ከተማ መሄድን አያውቅምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰነፍ ሥራ ያደክመዋል ወደ ከተማ መሄድ አያውቅምና። |
እንጀራ ላልሆነ ነገር ገንዘብን ለምን ታባክናላችሁ፥ የድካማችሁንም ዋጋ በማያጠግብ ነገር ለምን ትለውጣላችሁ? አድምጡኝ፥ በረከትንም ብሉ፥ ሰውነታችሁም በጮማ ደስ ይበለው።
እነዚህ ሁሉ፦ ለእርሱ ያልሆነውን ወደ እርሱ ለሚሰበስብ መያዣውንም ለራሱ የሚያበዛ ወዮለት! እስከ መቼ ነው? እያሉ ምሳሌ አይመስሉበትምን?