መክብብ 1:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠማማ ሊቀና አይችልም፥ የጐደለም ሊቈጠር ዘንድ አይችልም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተጣመመው ሊቃና አይችልም፤ የሌለም ነገር ሊቈጠር አይችልም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠማማው ሊቀና አይችልም፤ የሌለ ነገር ሊቈጠር አይቻልም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠማማ ይቀና ዘንድ አይችልም፤ ጐደሎም ይቈጠር ዘንድአይችልም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጠማማ ይቀና ዘንድ አይችልም፥ ጐደሎም ይቈጠር ዘንድ አይችልም። |
እግዚአብሔር የሚያደርገው ሁሉ ለዘለዓለም እንደሚኖር አወቅሁ፥ ምንም የሚጨመርበት ወይም የሚቀነስለት የለም፥ እግዚአብሔርም ሰዎች ይፈሩ ዘንድ አደረገ።
አውቅና እመረምር ዘንድ፥ ጥበብንና የነገሩን ሁሉ ትርጒም እፈልግ ዘንድ፥ ክፋትም አላዋቂነት፥ አላዋቂነትም እብደት እንደሆነ አውቅ ዘንድ እኔ በልቤ ዞርሁ።