ዘዳግም 9:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተን ካወቅሁበት ቀን ጀምሮ በጌታ ላይ ዓመፀኞች ነበራችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ እናንተን ካወቅኋችሁ ጊዜ ጀምሮ፣ በእግዚአብሔር ላይ እንዳመፃችሁ ናችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ካወቅኋችሁ ጊዜ ጀምሮ በእግዚአብሔር ላይ እንዳመፃችሁ ናችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእናንተ ከታወቀበት ቀን ጀምሮ በእግዚአብሔር ዐመፀኞች ነበራችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተን ካወቅሁበት ቀን ጀምሮ በእግዚአብሔር ዓመፀኞች ነበራችሁ። |
አልሰማህም፥ አላወቅህም፥ ጆሮህ ከጥንት አልተከፈተችም፤ አንተ ፈጽሞ ወንጀለኛ እንደሆንህ ከማኅፀንም ጀምረህ ተላላፊ ተብለህ እንደ ተጠራህ አውቄአለሁና።
እነርሱ ግን ዐመፁብኝ ይሰሙኝም ዘንድ አልወደዱም፥ ሁሉም እያንዳንዱ የዓይኑን ርኩሰት አልጣለም የግብጽንም ጣዖታት አልተወም፤ በዚህም ጊዜ፦ በግብጽ ምድር መካከል ቁጣዬን እፈጽምባቸው ዘንድ መዓቴን አፈስስባቸዋለሁ አልሁ።
ብቻ፥ በጌታ ላይ አታምፁ፤ ለእኛ እንደ እንጀራ ቁራሽ ናቸውና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሩ፤ ጥላቸው ከላያቸው ተገፍፎአል፥ ጌታም ከእኛ ጋር ነው፤ አትፍሩአቸው።”
ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የአሮንን በትር ወደ ምስክሩ ፊት መልሰህ አኑር፤ እርሱም ለሚያምፁብኝ ልጆች ምልክት ሆኖ ይቀመጥ፤ እነርሱም እንዳይሞቱ በእኔ ላይ ማጉረምረማቸውን ታስቆምበታለህ።”
“እናንተ አንገተ ደንዳኖች ልባችሁና ጆሮአችሁም ያልተገረዘ፤ እናንተ ሁልጊዜ መንፈስ ቅዱስን ትቃወማላችሁ፤ አባቶቻችሁ እንደ ተቃወሙት እናንተ ደግሞ።
እኔ ዓመፃችሁንና የአንገታችሁን ድንዳኔ አውቃለሁና፥ እኔም ዛሬ ከእናንተ ጋር ገና በሕይወት ሳለሁ እናንተ በጌታ ላይ ዐምፃችኋል፥ ይልቁንስ ከሞትሁ በኋላ እንዴት ይሆናል?
“ጌታ አምላክህ ከፊትህ ካስወጣቸው በኋላ፥ በልብህ፥ ‘እንድንወርሳት ወደዚች ምድር ጌታ ያስገባኝ በጽድቄ ምክንያት ነው’ አትበል፤ ጌታ እነዚህን ሕዝቦች ከፊትህ ያስወጣቸው ስለ ኃጢአታቸው ነው።